ግድባችን የአባይ ዘመን ትውልድ ትክክለኛ ሀሳብ፣ በትክክለኛ ጊዜ የገነባነው ዘመን ተሻጋሪ ቅርሳችን ነው ሲሉ በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ ቀይ አፈር ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
“ግድባችን አንድ ሆነን ብዙ፤ ብዙ ሆነን አንድ የሆንበት የሥብራታችን ማህተም ነው” ሲሉም የድጋፍ ሰልፈኞች ገልፀዋል።
የዘመናት ልፋታችን እውን ሆኗል። ነገም በርካታ በበሳል አመራር ሰጪነት የተያዙ ግዙፍ ውጥኖችን በሕብረት ጀምረንና ጨርሰን ዳግም ዓለም አቅማችንን እንዲገነዘብ በቁርጠኝነት ከመንግስት ጎን ቆመን እንሠራለን ብለዋል ሰልፈኞቹ።
የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ጋርሾ ለድጋፍ ሰልፈኞቹ ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት፤ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ከአብራኳ ከወጡ የቁርጥ ቀን መሪዎች በሳል አመራር ሰጭነት መላውን ህዝብ በአራቱም ማዕዘናት በማነቃነቅ እውን ሆኖ ወደ ሥራ በመግባቱ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።
በዘርና ቀለም ሳንለያይ በአንድ ሐሳብና አቋም በይቻላል መንፈስ ህዳሴን ማሳካታችን ኢትዮጵያዊያን ጀምረው የማይጨርሱት ግዙፍ ልማት አለመኖሩን ዓለም እንዲገነዘብ ትልቅ መልዕክት ሆኗል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
በሥራው የተሳተፉና አስተዋጽኦ ያበረከቱ አርብቶ አደሮች እና መላው የወረዳውን ማህብረሰብ በወረዳው አስተዳደር ስም አቶ ዮሐንስ አመስግነዋል።
በወረዳው መቀመጫ ቀይ አፈር ከተማ የተካሄደው የህዳሴ ግድብ የተለያዩ መልዕክት የያዙ መፈክሮች ታጅቦና በፀጥታ አካላት ሰልፍ ስነ-ሥርዓት እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተካሂዷል።
ህፃናትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የተሰማቸውን የደሰታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት ነው – የኮሬ ዞን አስተዳደር
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ2 ሺህ 291 ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ እና 112 ድልድዮች ይገነባሉ
የዘንድሮው የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በመደገፍ፣ በመተሳሰብ እና ያለውን ተካፍሎ በመብላት ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ