የዋቸሞ ዩንቨርስቲ አዲሱን ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 50 ቤተሰቦች ለበዓል መዋያ የሚሆን እህልና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
ድጋፍ የተደረገላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው የተሰጣቸው ድጋፍ በዓሉን ያለ ሀሳብ እንዲያሳልፉ ስለረዳቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ ዩንቨርስቲው ከመማር ማስተማር ስራ ጎን ለጎን በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዕለቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 50 ቤተሰቦች አዲሱን ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የበዓል መዋያ እንዲሆናቸው 50 ኪሎ ጤፍ፣ 3 ሊትር ዘይት፣የዶሮ እንቁላልና የልብስ ሳሙና ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን ከ380 ሺህ ብር በላይ እንደሆነም አመላክተዋል።
ተቋሙ የአረጋውያንና ሕጻናት ማዕከል ከመደገፍ ባለፈ በቀጣይም ተመሳሳይ ተግባር ለመፈጸም ቁርጠኛ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ሁሉም ሰው ካለው በማካፈል አብረው የማብላት ልማድ ማድረግ እንደለበትም ዶክተር ዳዊት መክረዋል።
ድጋፍ ከተደረገላቸው ማሕበረሰብ መካከል ወ/ሮ አማራች ቤያኮ እንደገለጹት ተፈናቃይ ከመሆናቸው የተነሳ ልጆቻቸውን ይዞ በከፍተኛ የኑሮ ችግር ውስጥ ባሉበት ወቅት የእህልና ምግብ ነክ ቁሳቁስ ድጋፍ መገኘታቸው እንዳስደሰታቸው ጠቁመዋል።
ሌሎች ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው ድጋፉ በዓሉን ያለ ሀሳብ እንዲያሳልፉ ስለረዳቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ጌታቸው መጮሮ ከሆሳዕና ጣቢያ

More Stories
ግብር ለአንድ ሀገር ህልውና መረጋገጥ እና ህብረተሰቡ ለሚያነሷቸው የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ወሳኝ በመሆኑ በአሰባሰብ ወቅት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
በሩብ ዓመቱ 3.7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ገለጹ
የማር ምርት እጅግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጎምቦራ ወረዳ በንብ ማነብ ስራ የተሠማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ