‎”ከምርታማነት በላይ እይታ ለሀገር ገጽታና ለኤክስፖርት እምርታ” በሚል መሪ ቃል የክልሉ ግብርና ቢሮ የፓናል ውይይት መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲላ ከተማ ተካሂዷል

‎”ከምርታማነት በላይ እይታ ለሀገር ገጽታና ለኤክስፖርት እምርታ” በሚል መሪ ቃል የክልሉ ግብርና ቢሮ የፓናል ውይይት መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲላ ከተማ ተካሂዷል

‎መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዲላ ከተማ ከንቲባ ዶክተር መስፍን ደምሴ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ብቸኛ የ13 ወራት ባለቤትና የሕብረብሔራዊነት ተምሳሌት መሆኗን ተናግረዋል።

‎ገዢው የብልግና ፓርቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በከተማው፣ በዞኑና በክልል ደረጃ በሁሉም የልማት መስኮች እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል በማለት ለውጡን ለማስቀጠል በርካታ ሥራዎችን እየተሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

‎ምርትና ምርታማነት በሁሉም ዘርፎችና በሁሉም አካባቢዎች በማረጋገጥ የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ ለመቀየርና የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመቅረፍ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ደረጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሪሁን ፍቅሬ ናቸው።

‎የክልሉ ሕዝብ የሚያነሷቸውን የልማት፣ የዕድገት፣ የመልካም አስተዳደርና ፍትሐዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎችን ለመመለስ መንግስት በቁርጠኝነት በመሥራት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

‎የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱንም በማዘመን የክልሉን ዕድገትና ልማት ለማፋጠን ሁሉም በየፊናው መረባረብ ይገባዋል ሲሉም አክለዋል።

‎የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ብዙ ብሔር፣ ቋንቋና ቱባ ባህል ያላት ሀገር መሆኗን ገልፀው መልካም የሆኑ ሀገራዊና የጋራ እሴቶችን ተንከባክቦ በማቆየት ለትውልድ ማሸጋገር እንደሚገባ አስረድተዋል።

‎ከግብርና ሥራ እንቅስቃሴዎች ጎን ለጎን በሁሉም ዞኖች የሚታየውን የአብሮነትና መረዳዳት እሴትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል።

‎በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስመዝገብ በምናደርገው ጥረት ልክ የትምህርት ጥራት ስብራትንም ለመጠገን ሁሉም አመራር የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎አያይዘውም የኑሮ ውድነት ፈተናዎችን ለመቋቋምና የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በወረዳው በሁሉም አካባቢዎች በሕብረተሰቡ ዘንድ ንቅናቄ በመፍጠር በተሠሩ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም አስገንዝበዋል።

‎በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከፓናል ውይይቱ በቂ ትምህርት እንዳገኙ ተናግረው፤ በክልሉ በየአካባቢው የተጀመረውን ሁለንተናዊ ዕድገት በማፋጠን ቀጣይነት ያለውን የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በመንግሥት እንደሀገር የተጀመሩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ከዳር ለማድረስ እንደሚደግፉ አብራርተዋል።

‎ዘጋቢ: እሥራኤል ብርሃኑ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን