በከተማው የሚገኙ እግር ኳስ ቡድኖች ተወዳዳሪና ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያደርጉት በጎ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የአርባምጭ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የአርባምንጭ ከተማ እርሻ ጤና እግር ኳስ ቡድን በአካባቢው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች የትምህርትና ለዘመን መለወጫ የሚሆን የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይለገብርኤል ሴኮ በከተማው ከሚገኙ የእግር ኳስ ቡድኖች ተወዳዳሪና ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት ባለፈ የተለያዩ በጎ ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀው፤ ይህ በጎ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም አመላክተዋል።
የልማት ቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ ፍሬው ካሳሁን፤ ቡድኑ ለአካባቢው ወጣቶች አርአያ ከመሆን ባለፈ በቀበሌው በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን እየደገፈ ይገኛል።
የእርሻ ጤና እግር ኳስ ቡድን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኝ ታምሩ እና አለማየሁ አላሮ፤ ቡድኑ ከተቋቋመ ጀምሮ ጤናማና በስነ-ምግባር የታነፁ ወጣቶች እዲወጡ እያደረገና የተለያዩ በጎ ተግባራትንም እያከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።
አንዳንድ ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በተደረገላቸው ሰብዓዊ ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው ድጋፍን ላደረጉላቸው አካላትንም አመስግነዋል።
ዘጋቢ፡ እንጃ ገልሲሞ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
በከተማው የሚገኙ እግር ኳስ ቡድኖች ተወዳዳሪና ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያደርጉት በጎ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የአርባምጭ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል