በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጷጉሜን 2/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ባለፈው በጀት አመት በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት መከናወናቸውን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ ገለፁ::
የቢሮው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚመክር የሴክተር ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ በጉባዔው መክፈቻ እንደገለጹት፥ ትራንስፖርት ሰዎችን ከእድሎቻቸው፣ ምርትን ከገበያ በማገናኘት የአንድ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ያፋጥናል::
የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ የመልካም አስተዳደር የተደራሽነት የመሰረተ ልማትና ሌሎችም ችግሮች ምርትና ምርታማነት እንዲቀንስና ለአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ አበርክቶ እንዳለው ጠቁመዋል::
የክልሉ መንግሥት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የዘገዩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በማድረግ ለአገልግሎት እንዲበቁ መደረጉን ተናግረዋል::
በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት መፈፀማቸውን የገለፁት ዶክተር መሀመድ የትራንስፖርት አገልግሎትን ምቹ ለማድረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሪፎርም መካሄዱን አስረድተዋል::
አንገብጋቢ የሆነውን የትራፊክ አደጋ ችግር ለመቅረፍ የተቋማት ክትትልና ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው የማህበረሰቡን የመንገድ አጠቃቀምና የደህንነት ንቃተ ህሊና ለማሳደግ የግንዛቤ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አክለዋል::
የመንገድ መሰረተ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ የፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓቱን በማጠናከር በቀጣይ በጀት አመት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን ዶክተር መሀመድ አስረድተዋል::
የህዝቡን ተሳትፎ በማሳደግ የመንገድ ተደራሽነት ማስፋት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል::
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው ትራንስፖርትና መንገድ ለሀገሪቱ እድገት ቁልፍ ሴክተር መሆኑን ገልፀው ክልሉ ህዝቡን በማስተባበር የመንገድ ልማትና ትራንስፖርቱን ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል::
በጉራጌ ዞንም ህዝቡን በማስተባበር በርካታ የመንገድና የድልድይ ግንባታዎች መከናወናቸውን አቶ ላጫ ተናግረዋል::
በጉባዔው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኖ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የዞንና ልዩ ወረዎች የዘርፉ ሀላፊዎች የትራንስፖርት ማህበራት የመንገድ ስራ ተቋራጮች ና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል::
ዘጋቢ፡ ሄኖክ ተክሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከልላዊ የሻይ ችግኝ ተከላ ስራን በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ አስጀመረ
ሰልጣኞችን ከስራ ጋር ለማስተሳሰር የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የብልጽግና ችቧችን ነው – አቶ እንዳሻው ሽብሩ