የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በወረዳው ቦጊንዳ ቀበሌ ተገኝተው ስራውን አስጀምረዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የሻይ ምርት በርካታ ተጠቃሚ ያለው ቢሆንም ስለተክሉና ስለልማቱ የማወቅ እድል ጠባብ ነበር ብለዋል።
ይህ ተክል ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ከገባ ከ80 ዓመታት በላይ ቢቆጠሩም፤ አሁን ላይ በክልሉ ያለው የማሣ ሽፋን ከ2 ሺህ 400 ሄክታር ያልበለጠ መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢኮኖሚ ጠቀሜታው ከፍተኛነት ትኩረት ሳይሰጠው እንደቆየ በመጠቆም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት በክልሉ ለማስፋፋት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በአርሶ አደሮች ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠር ወደስራ መገባቱንና መልካም ጅምር መታየቱን በማንሳት፤ የውሽውሽ ሻይ ልማት በክልሉ የተጀመሩ ስራዎችን እየደገፈ በመሆኑ አመስግነዋል።
ይህ ጅምር ስራ ለዘላቂ ተጠቃሚነት የሚያበቃ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ማስረሻ፤ በአሁኑ ወቅት በገዋታ ወረዳ ቦጊንዳ ቀበሌ በሚገኘው የችግኝ ጣቢያ ብቻ ከ150 በላይ ዜጎች የስራ እድል ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ይህንን ተጠቃሚነት በከፍተኛ ሁኔታና በዘላቂነት ለማስቀጠል መስራት እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።
በክልሉ 2.8 ሚሊዮን የሻይ ችግኝ ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን፤ እስካሁን 1.8 ሚሊዮን ችግኝ የሚተከልበት ፖሊ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
የተከላ መርሐ-ግብሩ በተጀመረበት ገዋታ ወረዳ ቦጊንዳ ቀበሌ ከ522 ሺህ በላይ የሻይ ችግኝ የሚተከልበት ፖሊ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ፤ አካባቢው ለሻይ ልማት ምቹ ቢሆንም የተገኘው ጥቅምና ስራው ያለበት ደረጃ ግን እምብዛም ነበር ብለዋል።
የአካባቢው ስነ-ምህዳር፣ የዝናብ ስርጭቱ፣ የአየር ንብረቱና የአፈሩ አሲዳማነት ለሻይ ተክል ምቹ እንደሆነ አብራርተዋል።
በዓለም ገበያ ላይ የኢትዮጵያ የሻይ ምርት ተፈላጊ መሆኑንና ወደ ውጭ ሀገራት ከሚላከው ውስጥ የክልሉ ድርሻ ሰፊ መሆኑን ተናግረዋል።
የሻይ ተክል አንዴ ከተተከለ በኋላ እስከ 70 ዓመት ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ ተክል መሆኑን አቶ አስራት ጠቁመዋል።
ስለዚህም ትኩረት ሰጥቶ በመስራት አካባቢን እና ሀገርን መጥቀም እንደሚገባ አሳስበዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡት የገዋታ ወረዳ ቦጊንዳ ቀበሌ ነዋሪዎች በተቋቋመው የሻይ ችግኝ ጣቢያ የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረው፤ በቀጣይነት ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሻይ ተክል ተስፋ ሰጪ መሆኑን በተሰጠው ግንዛቤ መረዳታቸውንና ወደ ስራ በመግባት ለውጤታማነት እንደሚተጉ ጠቁመዋል።
በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የግብርና ዘርፍ ባለሙያዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ ክፍሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከልላዊ የሻይ ችግኝ ተከላ ስራን በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ አስጀመረ

More Stories
ሰልጣኞችን ከስራ ጋር ለማስተሳሰር የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የብልጽግና ችቧችን ነው – አቶ እንዳሻው ሽብሩ
የደመወዝ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ ተገቢነት የሌለው መሆኑ ተገለፀ