የአርባምንጭ የድል ፋና የመጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን አንዳንድ በሆስፒታሉ ያገኘናቸዉ ተገልጋዮች ተናገሩ
አንዳንድ በሆስፒታሉ የሚታዪ የህክምና ቁሳቁሶች ጉድለት እንዲሟሉም ተገልጋዮቹ ጠይቀዋል።
አቶ ኃይሉ ዳንኤል ከኦሮሚያ ክልል ገላና ወረዳ ለህክምና የመጡ ሲሆን የሆስፒታሉ ባለሙያዎች በሚሰጡት አገልግሎት መደሰታቸዉን ገልፀዉ አገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱንም ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ ሲገለገሉ ያገኘናቸው ወ/ሮ አሰበች ዳኮማ እና አቶ አየለ ሆስፒታሉ አገልግሎት የሚሰጡ ባሉየዎች ከአቀባበል ጀምሮ በሚሰጠዉ አገልግሎት መርካታቸዉን ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ የአጠቃላይ ሀክም ዶ/ር ይድንቃቸዉ ሳሙኤል ተገልጋዮች በሆስፒታሉ ተገቢዉን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ሁሉም ባለሙያዎች በቅንነት እዲያገለግሉ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በሆስፒታሉ የሚስተዋሉ አንዳንድ የህክምና ቁሳቁሶችና የመድኃት እጥረት የበለጠ ተገልጋዮችን ለማርካት እንቅፋት መሆናቸዉንም ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ ሜድካል ዳይሬክተር ዶ/ር መታሠቢያ መለሰ ተቋሙ ከጤና ጣቢያ ወደ ሆስፒታል ካደገ ጊዜ ጀምሮ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠቱ የተገልጋይ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።
ተገልጋዮችን የበለጠ ለማርካት የቀዶ ጥገና ክፍል እና ተጨማሪ አልጋ ያስልጋል ያሉት ዶ/ሩ ሆስፒታሉ የሚሰጠዉን አገልግሎት በማስፋት በቅርቡ ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶች ወደ ሥራ እንደሚገቡ ገልፀዋል።
የሚስተዋለዉ የመድኃኒት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ከጋሞ ልማት ማህበር ጋር በመሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ዘጋቢ ፡ ካታንሾ ካርሶ
More Stories
በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሣ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ደም በመለገሳቸው በደም እጦት ምክንያት የሚሞቱ ወገኖችን ህይወት በማትረፋቸው መደሰታቸውን አስታወቁ
በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዙሪያ የሚደረገው ጥንቃቄ በመቀዛቀዙ አሁንም የቫይረሱ ስርጭት እየተስተዋለ መሆኑን ተገለጸ
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የጤናው ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አደረገ