የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለማጠናከርና ዘርፉን በማሳለጥ በኩል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኦሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለፀ
መምሪያው የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድና የኢትዮ ኮደርስ አፈፃፀም እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅዱን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዲመካ ከተማ ገምግሟል።
በመድረኩ በሳይንስና ፈጠራ ሥራ የተሳተፉ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የከተማና ወረዳ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደለ ጋያ እንደገለፁት፤ የዲጂታል ኢኮኖሚውን እውን ለማድረግ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን በማጠናከር ክፍተቶችን ለመቅረፍ የተጠናከረ የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ብሩክታዊት አኮ እንዳስረዱት፤ መምሪያው በበጀት አመቱ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰው በፈጠራ ሥራና በኢትዮ ኮደርስ የተመዘገበው ለውጥ እንዲቀጥልና ውጤታማ እንዲሆን ትኩረት እንደሚደረግ አስረድተዋል።
በመድረኩ የተሳተፋ አካላት እንደገለፁት በ2017 በጀት አመት የተስተዋሉ የባለሙያ ክፍተት፣ የሳይንስ ክበባት እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ፣ የኢትዮ ኮደርስ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና ሌሎች ድክመቶችን በመቅረፍ በ2018 በጀት ኣመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መድረኩ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በበጀት አመቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማትና ግለሰቦች የዋንጫና የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
አሰልጣኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲላበሱ እየተሠራ መሆኑ ተጠቆመ
በቴክኖሎጂ የተካኑ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት በመሥራት ሀገሪቱን ማበልጸግ እንደሚገባ ተገለጸ
በቴክኖሎጂና ፈጠራ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት የኢንዱስትሪ ሽግግርን በማፋጠን የሃገር ኢኮኖሚ እንዲያድግ እየሰራ መሆኑን በስልጤ ዞን የቂልጦ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ገለፀ