በቴክኖሎጂና ፈጠራ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት የኢንዱስትሪ ሽግግርን በማፋጠን የሃገር ኢኮኖሚ እንዲያድግ እየሰራ መሆኑን በስልጤ ዞን የቂልጦ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ገለፀ
ተቋሙ በአዲሱ አመት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በ2013 ዓ.ም የተመሰረተው እና በ65 ተማሪዎች እና በአራት የትምህርት ክፍሎች ስራውን የጀመረው የቂልጦ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አሁን ላይ ከ3 መቶ በላይ ሰልጣኞች እንደሚገኙ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ አብዱ ረዲ ናቸው።
ኮሌጁ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራና በኢንዱስትሪ ሽግግር ብሎም ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ሲሆን ለዚህም ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን ስልጠና ከመስጠት ባለፈ ሰልጣኞች በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ በግላቸው ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የኮሌጁ ዲን አክለው ገልፀዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ ከኮሌጁ ምስረታ ጀምሮ በርካታ ድጋፎችን በማድረግ ላይ መሆኑን የገለፁት ዲኑ፤ ለዚህም ማሳያው 10 ኮምፒውተሮችን፣ ፕሮጀክተሮችን፣ ጀነሬተር እና ሰባት ሄክታር መሬት በመለገስ በጥቅሉ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
በ2018 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን በመቀበል የተለያዩ ሙያ ባለቤቶች ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ሲሆን በተለይም በማህበረሰቡ ዘንድ ለቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች ያለው የተሳሳተ እሳቤ በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀየር የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር በወረዳው ባሉ ቀበሌያት ሁሉ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን አመላክተዋል።
በተቋሙ የሚሰጡ ስልጠናዎች በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገራትም ተመራጭ እየሆኑ ይገኛል ያሉት ዲኑ፤ ተማሪዎች የእድሉ ተጠቃሚ በመሆን የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ ሃጀራ ግርማ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለማጠናከርና ዘርፉን በማሳለጥ በኩል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኦሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለፀ
ለዜጎች በሶላር ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ስልጠና በመስጠት ዘርፉ ላይ ተጠቃሚነታቸውን ለማጎልበት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ
በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ተግባራዊ በማድረጋቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን በየኪ ወረዳ የኩቢጦ አካባቢ አርሶአደሮች ተናገሩ