በዳውሮ ዞን የሎማ ቦሣ ወረዳ ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከ404 ሚሊየን 249 ሺህ ብር በላይ በጀት አጸደቀ
በዳውሮ ዞን የሎማ ቦሣ ወረዳ ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት 404 ሚሊየን 249 ሺህ 143 ብር በጀት አጽድቋል፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዘለቀ ሲሳይ፤ የወረዳው አስተዳደር የወረዳውን ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና ሥረ-ነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ለመተግበር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የአደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ህብረተሰቡን በየደረጃው ተጠቃሚ ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተዋል።
የወረዳውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ስትራቴጂክ ዕቅድ በማዘጋጀት እንዲሁም በመገምገም ተግባራዊ ያልሆኑና የተለዩ ቀሪ ስራዎችን በበጀት ዓመቱ ትኩረት በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ ከሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚጠበቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከምክር ቤቱ አባላት ገቢ አሰባሰብን ጨምሮ በትምህርት፣ በመልካም አስተዳደርና ከመሠረተ ልማት ማሟላት ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች የየሴክተር መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና ከወረዳው አስተዳዳሪ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ጉባኤው ለሁለት ቀናት በነበረው ቆይታ በቀረቡት ሪፖርቶችና በ2018 በጀት የመከረ ሲሆን አዲስ ሹመት በመስጠት ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ አሸናፊ ግዘው – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
በመኸር እርሻ ከሚለሙ ስብሎች ጥሩ ምርት ለማግኘት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ እንደሚገኙ በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሣ ወረዳ የሚገኙ አርሶአደሮች ተናገሩ
ነጋዴው ማህበረሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ሳይሸበር ኑሮን በማረጋጋት ለመንግስት ያለውን አጋርነት ሊያረጋግጥ እንደሚገባ በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት ስራ ማስፈፅሚያ 5 ቢሊዬን 108 ሚሊዬን ብር በላይ በጀት አፅደቀ