የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማሳለጥ የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱና በታማኝነት እንደሚከፍሉ አንዳንድ የአርባምንጭ ከተማ ነጋዴዎች ተናግረዋል።
አንዳንድ የአርባምንጭ ከተማ ነጋዴዎች፤ የአርባምንጭ ከተማን ዕድገት ለመደገፍ እና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስ የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ በመክፈል ግዴታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በግብር አሰባሰብ ሂደት የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በማረምና ወቅቱን የጠበቀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በቀጣይ መሰጠት እንደሚጠበቅ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ በረከት ማቲዮስ፤ በ2018 በጀት አመት በ5 ወራት ውስጥ 1 ቢሊየን 5 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉንና የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የተለያዩ ተግዳሮቶች እንደነበሩ አስረድተዋል።
አቶ በረከት አክለውም፤ ከአዲሱ የገቢ ግብር አሰባሰብ ጋር በተያያዘ በግብር አከፋፈል ላይ የሚስተዋሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመቅረፍ መስሪያ ቤቱ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን እየሰጠ እንደሆነም ጠቁመዋል።
የግብር ስወራን ለመከላከልና ተገቢዉን ግብር በወቅቱ ባልከፈሉት ግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነም አስታውቀዋል።
የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማሳለጥ ሁሉንም የገቢ ግብር ርዕሶችን አሟጦ በመጠቀም የገቢ መጠንን በማሳደግ ረገድ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተቋሙና በግብር ከፋዩ ዘንድ የበለጠ ቅንጅታዊ አሰራርን ለመዘርጋት እየተሰራ እንደሆነም አቶ በረከት ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ስምረት አስማማው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ