በሁሉም ዘርፎች እንደሀገር አመርቂ ውጤቶች እየተዘመገቡ ነው – የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች
ሀዋሳ፡ ታኅሣሥ 05/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሁሉም ዘርፎች እንደሀገር አመርቂ ውጤቶች እየተዘመገበ መሆኑን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
“የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል ከቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ሀገራዊ የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
የህዝብ ጥያቄዎች በአግባቡ ተይዘው ምላሽ እየተሰጠባቸው መሆኑ የሚመሰገን መሆኑን ገልጸው፥ ሌሎች ሀገራዊ ጥያቄዎችንም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ምላሽ ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አበረታች ነው ብለዋል፡፡
ክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ትሩፋት መሆኑን ገልጸው፥ በቦንጋ ከተማ የተገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ እንዲሁም አዳሪ ትምህርት ቤት ምላሽ ማግኘቱ የሚያስመሰግን እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ በሌማት ትሩፋት የተጀመሩ ሥራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የተጀመረው ሥራ ሁሉን ያሳተፈና ውጤታማ መሆኑን የገለጹት የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች፥ በሁሉም ዘርፎች እንደሀገር አመርቂ ውጤቶች እየተዘመገበ መሆኑን ተመልክተና ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በኮሪደር ልማት የተሰሩ ሥራዎች በዓለም አደባባይ ኢትዮጵያ ትኩረት እንድታገኝ አስችለዋል ብለዋል፡፡
በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘርፍም ያለው ሥራ አመርቂ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በሀገር ደረጃ ከተመዘገቡ ስኬቶች የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎችም ተቋዳሽ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡
በሌላ በኩል የቦንጋ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ፣ በቦንጋ ከተማ የአስፋልት መንገድ ብልሽት፣ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ በቀጣይ ምላሽ ሊሰጥባቸው ይገባል ሲሉ ጠይቀው፥ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፍጆታ የታሪፍ ጭማሪ ሊታይ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ክልሉን የሚያገናኙ የተለያዩ መንገዶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲከናወኑ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡
የካፋ ዞን ደንን ጠብቆ ያቆየ እንደመሆኑ መጠን ማህበረሰቡ ከደኑ መጠቀም እንዲችል መደረግ አለበት ሲሉ አንስተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ዳንኤል መኩሪያ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል