የቡርጂ ዞን መንግስት ሰራተኞች የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ብዙዎችን የቤት ባለቤት ማድረግ በመቻሉ፥ አባላቱ የቁጠባ መጠናቸውን በማሳደግ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
ማህበሩ ብዙዎችን የቤት ባለቤት በማድረጉ አባላቱ የቁጠባ መጠናቸውን በማሳደግ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲል የቡርጂ ዞን አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
የቡርጂ ዞን መንግስት ሰራተኞች የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር 7ኛ ዙር 5ኛ መደበኛ ጉባኤ አካህዷል።
በጉባኤው ማህበሩ ያስገነባው የጽ/ቤት ህንጻ ተመርቋል።
የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ በጉባኤው መክፈቻ ንግግራቸው፣ ማህበሩ ብዙዎችን የቤት ባለቤት ማድረጉን አንስተው አባላቱ የቁጠባ መጠናቸውን በማሳደግ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አከባቢያችንን ለመለወጥ አንድነታችንን ማጠናከር አለብን ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የመንግስት ሰራተኞችም ልዩነቶችን በመተው አንድ ሊያደርጉን የሚችሉ ሀሳቦች ላይ ተስማምተን መሥራት አለብን ብለዋል።
አብዛኞቹ አባላት ለአገልግሎት ብቻ እንደሚመጡ ያነሱት የማህበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘርቆ ኮኔ ለማህበሩ ያለንን ግንዛቤ በማሳደግ በቁርጠኝነት መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ያለ ተግባር ዕድገት የለም ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፥ ማህበሩን ቀጣይ ወደ ባንክ ለማሳደግ በትኩረት ልንሠራ ይገባል ብለዋል።
የ2016/17 ዓ.ም የሥራ እና የኦዲት ሪፖርት ላይ በመወያየት የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ የተለያዩ ውሳኔዎች ቀርበው አባላቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።
ዘጋቢ: አሀዱ አሸናፊ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ከመማር ማስተማር ተግባር ባለፈ የአካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አስታወቀ
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) መጭው ጊዜ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን የምንሸጋገርበት ብሩህ ዘመን መሆኑን ተናገሩ
በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ