የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የጤናው ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አደረገ
በመድረኩ ባለፈው በጀት ዓመት በውጤትና በጉድለት የተከናወኑ አበይት ተግባራት ዙሪያ ሰነዶች ቀርበው የጋራ ውይይት ተደርጓል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ በመምሪያው የስራ አፈፃፀም ላይ በመወያየት የተሻሉ ልምዶችን ለማጎልበትና ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችል ሀሳብና አቅጣጫ አስቀምጠዉ፤ በተለይ በጉድለት ከተመዘገቡ ተግባራት በመንግስትም ሆነ በአጋር ድርጅቶች የሚቀርቡ ግበዓቶችን በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ ማባከንና ለኪራይ ተጋላጭ እንዲሆኑ የማድረግ አዝማሚያዎች ስላሉ በቀጣይ ዘርፉን በልዩ ትኩረት መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ ኦርዮን ኦይሻ በበኩላቸዉ፤ በበጀት አመቱ በአንዳንድ መዋቅሮች በእናቶች ወሊድ አገልግሎት እና በህፃናት ክትባት ላይ የተሻሉ አፈፃፀሞች ቢመዘገብም ከጥራት አንፃር መሰረታዊ ችግሮች ያሉባቸዉ መሆን፣ የላብራቶሪ ባለሙያዎችና የግበዓት እጥረት ማህበረሰቡን በማሳተፍ ወረርሽኞችን መከላከል እንዲሁም በመረጃ አያያዝ እና ሌሎች በጉድለት የተመዘገቡና ትኩረት የሚሹ ተግባራት በመኖራቸዉ በቀጣይ መዋቅሮች እያንዳንዱን ተግባራት ጥራትን መሰረት አድርገዉ በትኩረት መስራት እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ የኛንጋቶም እና የማሌ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ በርቂ እና አቶ ማናሌ መኮ በሰጡት እተያየት፤ በጥንካሬ የተመዘገቡ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል በጉድለት የተመዘገቡ ተግባራትን በዝርዝር በመለየት በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የዞን፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የሥራ ኃላፊዎች የጤና ኤክስቴንሽኖች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የእውቅና መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የጤናው ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አደረገ

More Stories
በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዙሪያ የሚደረገው ጥንቃቄ በመቀዛቀዙ አሁንም የቫይረሱ ስርጭት እየተስተዋለ መሆኑን ተገለጸ
እድሚያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የአንጀት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ
የጤና ሚኒስቴር 4.2 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የህክምና መሣሪያዎች ለክልልና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ድጋፍ አደረገ