በጋሞ ዞን የዘፍኔ ከተማ አስተዳደርነት መዋቅር መፈቀዱ ለከተማ ዕድገት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ
የከተማው አስተዳደሩ በበኩሉ የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፆ ህዝቡ ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ በሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የልማት ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆናቸውን የገለፁት የዘፍኔ ከተማ ነዋሪ አቶ መሸሻ ማዳ በተለይም አሁን ላይ የከተማ አስተዳደር መዋቅር ተፈቅዶ ወደ ሥራ መገባቱ የልማት ጥያቄን ለመመለስ ትልቅ አጋጣሚ ፈጥሯል ብለዋል።
አቶ ገረሱ ዳርጫ ሌላኛው የከተማው ነዋሪ ሲሆኑ የከተማ አስተዳደር መፈቀዱና ወደ ሥራ መገባቱ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
መምህርት ሰላምነሽ ሲሳይ በበኩላቸው ለሥራ አጥ ወጣቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ የሚኖረው ጠቀሜታ ትልቅ ነው ብለዋል።
የዘፍኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መለሰ ማርካ ህብረተሰቡ አገልግሎት በቅርበት ማግኘት እንዲችል የከተማ አስተዳደር መዋቅር መፈቀዱ በዋናነትም የህዝብ ጥያቄ ፍትሐዊና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ምላሽ እንዲያገኝ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል ።
በቀጣይ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ህዝቡ ከአስተዳደሩ ጎን እንዲሆን ከንቲባው ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ታምሩ በልሁ ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
በሩብ ዓመቱ 3.7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ገለጹ
የማር ምርት እጅግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጎምቦራ ወረዳ በንብ ማነብ ስራ የተሠማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሰ የግብርና ልማት ላይ አደጋ እንዳያስከትል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ