ባለፉት 6 ወራት ለ235ሺ 205 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገለጸ
ሀዋሳ: ጥር 25/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ባለፉት 6 ወራት ለ235ሺ 205 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለፁ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
ባለፉት 6 ወራት ለ235ሺ 205 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገለጸ
በክልሉ ለዜጎች ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል ለመፍጠር በየአካባቢው ያለውን እምቅ ሀብት እና ፀጋዎችን ለይቶ በዕውቀት፣ በሥራ ፈጠራ ሀሳብና በክህሎት የተመራ ስራ በመፍጠር የዜጎች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ርብርብ መደረጉ ለምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ለ400ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በግማሽ አመት አፈፃፀም የዕቅዱን 98 በመቶ በማሳካት ለ235ሺህ 205 ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ መሆናቸው አስረድተዋል፡፡
የማምረቻና መሸጫ ቦታ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለኢንተርፕራይዞች በማቅረብ እና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ለአምራች ዘርፍ ከተሰሩ ሼዶች ያልተላለፉ 786 ሼዶችን በመለየት ከነዚህ ውስጥ 241 ሼዶችን በማስመለስ በህጋዊ መንገድ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ በተለያዩ የልማት ስራ ተጠቃሚ የሆኑ ከ60ሺህ በላይ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፥ በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት 48ሺህ 734 ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የግብርና ስራዎችን ተመለከተ