በዓለም አቀፍ ደረጃ በዕውቀትና ክህሎት ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮምፒውተር ዕውቀትና ክህሎት ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።
በከተማ አስተዳደሩ በሦስት ዓመታት ውስጥ ከ9 ሺህ 800 በላይ ሠልጣኞችን ለማሠልጠን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የከተማው ሳይንስ ኢንፎርሜሽና ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታውቋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የ5 ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የክረምት ወራት ማስጀመሪያ ንቅናቄ መርሃ ግብር በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የዲላ ከተማ አስተዳደር ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኢሳያይስ ተፈራ የኮደርስ ሥልጠና ዜጎች በአገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በ3 ዓመታት ውስጥ ኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠናን 9 ሺህ 885 ሠልጣኞች ለመስጠት ታቅዶ እየተሠራ ነው ያሉት አቶ ኢሳይያስ፥ በ2017 በጀት ላይ 1 ሺህ 951 ኦንላይን ተመዝግበው ሥልጠና እየወሰዱ ካሉት ውሰጥ 400 ሠልጣኞች ሥልጠናውን ማጠናቃቸውን አብራርተዋል ።
ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ኢትዮ ኮደርስ ሥልጠን ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልጸው፥ በዚህ ክረምት ወራት ላይ ደግሞ 3 ሺህ ሠልጣኞች ኦንላይን ተመዝግበው እንዲሠለጥኑ ለማስቻል የንቅናቄ ሥራ በስፋት እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
መድረኩን የከፈቱት የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) በጠቅላይ ሚኒስትርና አብይ አህመድ(ዶ/ር) የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ዲጅታል ኢኮኖሚን ለመገንባት፣ የዜጎችን ዕውቀትና ክህሎት የሚያጎለብት ሥልጠና መሆኑን አስረድተዋል።
ዓለም ወደ ዲጅታላይዜሽን እየመጣች ያለበችበት ወቅት በመሆኑ ይህን ሥልጠና ደግሞ አገራችን ወደዚህ ሥርዓት ለመሸጋገር የምታደርገውን ጉዞ በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ዶክተር መስፍን አስረድተዋል፡፡
ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ በነፃ የሚሰጠውን ሥልጠና ሁሉም እንዲወስድ መልዕክት ያስተላልፉት ከንቲባው፥ አሁን የተመዘገበውን ዝቅተኛ አፈጻጸም ለማሻሻል በከተማው በሁሉም አደረጃጀቶች ላይ በትኩረት ሊመራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊና የኢትዮ ኮደርስ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ታሪኩ በየነ፥ የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን በማፍራት ቴክኖሎጂ የሥራ መሳርያ ብቻ ሳይሆን የለውጥ አራማጆችን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።
በከተማው የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ዓመታዊ ማጠቃለያ ጉባኤ በማካሄድ የዓመቱን አፈፃፀም በጥልቀት በመገምገም በክረምት ወራት ላይ አፈፃፀሙን የተሻለ ለማድረግ የንቅናቄ ሥራ በስፋት እንዲሠራ አቅጣጫ ተቀምጣል።
በዓመቱ የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ላጠናቀቁ ሠልጣኞችም ሴርትፊኬት ተሰጥቷቸዋል።
ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ጎበና – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሽከርካሪዎች ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን የወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ገለፀ
የቴክኖሎጂ ዘርፍ በየጊዜው እየተፋጠነ ባለበት በዚህ ወቅት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፎች ወሳኝ መሆናቸውን የምስራቅ ጉራጌ ዞን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ገለፀ
በማህበረሰቡ ዘንድ ይስተዋሉ የነበሩ ነባር ችግሮችን መቅረፍ የቻሉ ቴክኖሎጂዎች እያቀረበ መሆኑን የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ