ሀብት ያካበቱ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር
በደረሰ አስፋው
እንደ ሀገር የድህነት ምጣኔን ለመቀነስና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የስራ ዕድል ፈጠራ የማይተካ ሚና ያበረክታል፡፡ በርካታ ወጣቶችን በየአካባቢያቸው ያሉ የስራ ዕድል አማራጮችን በመጠቀም የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡
በዚህም በየአመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል እየተፈጠረላቸው ነው፡፡ ካለው የስራ አጥ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር የተፈለገው ደረጃ ላይ ተደርሷል ባይባልም ሀገሪቱ ካላት ውስን ሀብት አኳያ አፈጻጸሙ አበረታች እንደሆነ መታዘብ ችለናል፡፡
ለአብነት ያደረግነውም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸምን ነው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በበጀት ዓመቱ የክልሉን ስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል ባለቤት ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ነው ከክልሉ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
በክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራን ክህሎት መር በማድረግ ሀብት ያካበቱ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር እየተሰራ ያለው ስራም ውጤት እየታየበት ነው፡፡
የሥራ ዕድል ፈጠራው ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታትም አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡ በክልሉ የሚገኙ ሥራ አጦችን በመለየት እና ወደ ስራ በማስገባት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ነው የተመላከተው፡፡
ከማስፈጸም አቅምና ከስራ ፈላጊዎች አመለካከት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ስልጠና በመስጠት ዜጎችን ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የማድረግ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በዛብህ በላይነህ፣ ወጣቶች በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ አመለካከትን ከመቅረጽ ጀምሮ መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ፍላጎትንና ገበያን ማዕከል ያደረገ ስልጠና ከመስጠት አኳያም ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ይናገራሉ። ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት በበጀት አመቱ መጀመሪያ በክልሉ የሚገኙ ሥራ አጦችን በመለየት እና ወደ ስራ በማስገባት ሂደት የተቀናጀ ስራ መሰራቱንም ይገልጻሉ፡፡
የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ በዛብህ የበጀት አመቱን የስራ ክንውን አስመልክተው ለንጋት ጋዜጣ በሰጡት ማብራሪያ በበጀት አመቱ መጀመሪያ በገጠርና በከተማ የስራ አጥ ልየታ ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን ነው የተናገሩት፡፡
በዚህም በክልሉ በአመቱ መጀመሪያ በገጠርና በከተማ የስራ አጥ ልየታ መደረጉን ገልጸው፣ በገጠር 142 ሺህ 589 ወጣቶችን ለመለየት ታቅዶ 176 ሺህ 556 ስራ አጥ ወጣቶችን በመለየት የዕቅዱን መቶ ከመቶ በላይ ማሳካት እንደተቻለ ጠቁመዋል፡፡
በተመሳሳይ በከተማ 158 ሺህ 231 ወጣቶችን ለመለየት ታቅዶ 159 ሺህ 413 ወጣት ስራ ፈላጊዎችን መለየት ተችሏል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ እንደ ተቋም በገጠርና በከተማ 300 ሺህ 820 ስራ ፈላጊዎችን ለመለየት ታቅዶ 335 ሺህ 969 በመለየት ከእቅዱ በላይ ተከናውኗል ብለዋል፡፡
በገጠርና በከተማ በተፈጠረው የስራ ዕድል በቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በርካታ ወጣቶች የስራ ዕደል እንደተፈጠረላቸው አቶ በዛብህ ገልጸው፣ በዚህም በቋሚ የስራ ዕድል በገጠር 91 ሺህ 256 ታቅዶ 97 ሺህ 476 የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ በከተማ 101 ሺህ 258 ታቅዶ 103 ሺህ 058 የስራ ዕድል ተፈጥሯል ነው ያሉት።
በአጠቃላይ በገጠርና በከተማ በቋሚ የስራ ዕድል ለመፍጠር የታቀደው 205 ሺህ 234 ሲሆን ክንውኑ 212 ሺህ 330 መሆኑን አንስተው ከዚህም የሴቶች ድርሻ 43 በመቶ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ውጭ የውጭ ሀገር የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው 8 ሺህ 689 ናቸው፡፡ በቋሚ የስራ ዕድል ከተሰማሩት ውስጥ የግብርናው ዘርፍ 32 በመቶ፣ የኢንዱስትሪው ድርሻ 23 በመቶ እና የአገልግሎት ዘርፉ ድርሻ ደግሞ 45 በመቶ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ከጊዜያዊ የስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ አቶ በዛብህ እንደገለጹት ደግሞ በገጠር 22 ሺህ 814 ታቅዶ 48 ሺህ 787 የተከናወነ ሲሆን በከተማ 25 ሺህ 318 ታቅዶ 24 ሺህ 228 ተከናውኗል። በጠቅላላው በገጠርና በከተማ በጊዜያዊ የስራ እድል 48 ሺህ 132 ታቅዶ 73 ሺህ 015 ጊዜያዊ የስራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በበጀት አመቱ በክልሉ በቋሚና በጊዜያዊ የስራ ዕድል ለማሳማራት የታቀደው 253 ሺህ 366 ሲሆን ክንውኑ 285 ሺህ 393 ነው፡፡ በዚህም ወንድ 226 ሺህ 683 ሲሆን ሴት 126 683 ነው፡፡ 285 ሺህ በድምሩ 285 ሺህ 393 ወጣቶች በጊዜያዊና በቋሚ ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡
ከስምሪት አኳያ የሴቶች ሽፋን 43 በመቶ ነው። አፈጻጸሙም ያለፈው አመት ዝቅተኛ እንደነበር አስታውሰው በ2017 የበጀት አመት ግን የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበበት እንደሆነ መገምገሙን ነው ያሳወቁት፡፡
በአብዛኛው የስራ ዕድል የተፈጠረባቸው የስራ ዘርፎች ማኑፋክቸሪንግ፣ እንዲሁም የብረታ ብረትና እንጨት ምርቶችን በማምረት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የመተካት ስራ ተሰርቷል። በአገልግሎት በሻይ ቡና፣ በመጠጥ፣ በምግብ ቤቶችና በሌሎችም፣ በግብርና ዘርፍ ፍራፍሬ ልማት እና በተለያዩ ሰብሎች ማምረት የተሰማሩ ሰፊውን ሽፋን የሚወስዱ የስራ ዘርፎች እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡
የበጀት አመቱን የቢሯቸውን የስራ ክንውን አስመልክተው ሌላው አቶ በዛብህ የገለጹት የብድር ስርጭት እና አመላለስን በተመለከተ ነው፡፡
በዚህም በአመቱ በመጀመሪያ በማህበር ተደራጅተው ወደ ስራ ለሚገቡ ቁጠባ ቀዳሚ ተግባር እንደሆነ አንስተው በአመቱ ወደ ስራ የሚገቡ ስራ ፈላጊዎች 314 ሚሊዮን 424 ሺህ 099 ብር ለማስቆጠብ ታቅዶ 328 ሚሊዮን 066 ሺህ 054 ብር በማስቆጠብ መቶ ከመቶ በላይ የሆነ አፈጻጸም ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡
ከቁጠባ ጎን ለጎን የሚከናወነው ብድር ለማስመለስ እንደሆነ አንስተው በዚህም 714 ሚሊዮን 044 ሺህ 025 ሺህ ብር ብድር ለማስመለስ ታቅዶ 539 ሚሊዮን 060 ሺህ 270 ብር ማስመለስ ተችሏል ብለዋል፡፡
ከተመለሰው ውስጥ 84 ሚሊዮን 290 ሺህ 022 ብር በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከደቡብ ካፒታል ሊዝ ማሽን ዕዳ የተመለሰ ሲሆን ቀሪው በኦሞ ባንክና በሌሎች የብድር ማይክሮ ፋይናንሶች የተሰራጨና የተመለሰ 445 ሚሊዮን 470 ሺህ 248 እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጋር የአፈጻጸም ጉድለት ሆኖ የታየው በየደረጃው ያለው የብድር አስመላሽ ግብረ ሀይል በየጊዜው ሂደቱን እየገመገመና የቀጣይ አቅጣጫ እያስቀመጠ ያለመሄድ ችግር የታየ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የብድር ስርጭት ወደ ስራ ለሚሰማሩት መነሻ ካፒታል በመሆኑ በበጀት አመቱ በክልሉ 1 ቢሊዮን 340 ሚሊዮን 556 ሺህ 584 ብር ብድር ለማሰራጨት ታቅዶ 833 ሚሊዮን 123 ሺህ 717 ብር ተሰራጭቷል፡፡
ከዚህ ውስጥ 237 ሚሊዮን 924 ሺህ 882 ብር በሊዝ ማሽን እና ለስራ ማስኬጃ የቀረበ ሲሆን ሌላው በኦሞና በሌሎች ባንኮች የተሰራጨው 595 ሚሊዮን 198 ሺህ 835 ብር በአመቱ ለስራ ፈላጊዎች የተሰራጨ ብር ነው ብለዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የማምረቻና መሸጫ ሼዶችን ከማመቻቸት አንጻር ጥሩ ውጤት የተገኘበት እንደሆነ የገለጹት አቶ በዛብህ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራው የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ በክልሉ ሁለንተናዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም አመልክተዋል።
በዚህም ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተሰጠው የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በእያንዳንዱ የገጠር ቀበሌያት 6 ሄክታር መሬት እና በእያንዳንዱ የከተማ ቀበሌያት 1 ሄክታር መሬት እንዲዘጋጅ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡
በዚህም በአመቱ 5 ሺህ 694 ሄክታር መሬት ለማዘጋጀት ታቅዶ 7 ሺህ 205 ሄክታር መሬት በማዘጋጀት የዕቅዱን መቶ ከመቶ በላይ ማሳካት እንደተቻለ ነው ለጋዜጣዋ ሪፖርተር የገለጹት፡፡
ከሼድ ግንባታ ጋር በተያያዘ በአመቱ 271 ሼዶችን ለመገንባት ታቅዶ 300 ሼዶችን መገንባት ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ 275 ሼዶችን ለማስመለስ ታቅዶ 436 ሼዶችን ማስመለስ ተችሏል ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ በበጀት አመቱ ከሼድ አቅርቦት ጋር በተያያዘ አዳዲስ የተገነቡ እና የተመለሱትን ጨምሮ 546 ታቅዶ 736 ሼዶችን ማዘጋጀት ተችሏል ብለዋል፡፡
የስራ ዕድል ለተፈጠረላቸው ወጣቶች የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር እና በውጭ ሀገር የገበያ ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተለይ በሀገር ውስጥ ድጋፍ 1 ቢሊዮን 799 ሚሊዮን 472 ሺህ 354 ብር የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ 2 ቢሊዮን 78 ሚሊዮን 278 ሺህ 996 ብር በሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
ከውጭ ሀገር ገበያ ድጋፍ ጋር በተያያዘ በ6 ኢንተርፕራይዞች ወደ 2 ሚሊዮን 218 ሺህ 619 ዶላር ለማቅረብ እና ለማገናኘት ታቅዶ በ10 ኢንተርፕራይዞች ተከናውኗል፡፡ በዚህም 795 ሺህ 922 ዶላር በማገናኘት የውጭ ሀገር ምንዛሬ ማግኘት የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙም 77 በመቶ ላይ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
በክልሉ 38 ባዛር ኤግዚቪሽኖች ለማዘጋጀት ታቅዶ 40 ተከናውኗል፡፡ የሂሳብ ዝርጋታን በተመለከተ 19 ሺህ 357 ታቅዶ ክንውኑ 16 ሺህ 442 ሲሆን አፈጻጸሙ 85 በመቶ፣ የኦዲት ዝርጋታ ደግሞ 568 ታቅዶ አፈጻጸሙ ወደ 87 በመቶ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
የደረጃ ሽግግርን በተመለከተም ሞዴል የሆኑትን መምረጥ እና ማሸጋገር አስፈላጊ በመሆኑ 3 ሺህ 371 ለማሸጋገር ታቅዶ 2 ሺህ 618 ማሸጋገር ተችሏል፡፡ የሞዴል መረጣ እና ተሞክሮ ቅመራን በተመለከተ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክተው በሰጡት ገለጻ ሞዴል መረጣ 300 ታቅዶ 262፣ እንዲሁም ተሞክሮ ቅመራ 134 ታቅዶ 164 መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
ከአንድ ማዕከል ጋር በተያያዘ ሞዴል ማዕከላትን ከመፍጠር አኳያ 96 አንድ ማዕከላትን ለማጠናከር ታቅዶ 108 ተከናውኗል። አፈጻጸሙም መቶ ከመቶ በላይ ነው ብለዋል፡፡
በበጀት አመቱ ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ አቶ በዛብህ እንዳሉት ከኦሞ ባንክ ጋር በተያያዘ የብድር አቅርቦት ችግር በዋናነት የሚጠቀስ እንደሆነ አንስተው፣ በተለይ ከ50 ሺህ ብር በላይ ብድር ለሚወስዱ ኢንተርፕራይዞች ከወረዳና ከከተሞች ወደ ዞን ጸድቆ ከተላከ በኋላ የአሰራር መጓተት ጊዜ የሚወስድበት ሁኔታ በችግርነት የታየ ነው፡፡ በተመሳሳይ የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ በግብርና ዘርፍ ለሚሰማሩትም የግብአት አቅርቦት ችግር እና በቂ መሬት ያለማግኘት ችግር ስራ አጦችን ወደ ስራ በማስገባቱ ሂደት ተግዳሮቶች እንደነበሩ ነው ያመለከቱት፡፡
እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ፣ በስልክና በአካል በመገኘት የመደገፍ ስራ ተሰርቷል፡፡ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ጋር ተቀራርቦ በመስራት ችግሮችን የመፍታት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ደረጃም ለጉዳዩ ያልተቋረጠ ክትትል በማድረግ ዘርፎችን ክትትል በማድረግና በየጊዜው እየገመገሙ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማረም የሰሩት ስራም በበጀት አመቱ ለአፈጻጸሙ ማደግ ጉልህ አበርክቶ ማድረጉንም ነው የተናገሩት፡፡
ለወጣቶች የግንዛቤ ስልጠናዎችን ከመስጠት አኳያም እንዲሁ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ላይ ከቴክኒክና ሙያ ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ የሚሰማሩት የቅድመ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ለማህበረሰቡ፣ ወጣቱ፣ አመራሩና ባለሙያው በአመለካከት ደረጃ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንደተሰጡም ነው የተናገሩት፡፡
More Stories
የወላጆች ቀን እና አንዳንድ ወላጆች
በርካታ የቀለም ልጆችን ያፈሩ መምህርት
“አካል ጉዳተኛ ተቀባይ ብቻ አይደለም ሰጪም ነው” – አቶ ልብአገኘሁ ገ/ማሪያም