በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የአርባምንጭ ደምና ህብረህዋስ ባንክ በ2017 በጀት አመት ከ6 ሺህ 378 ዩኒት በላይ ደም መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ
ጠንካራ ተግባራትን በማጠናከር ጉድለቶችን በማረም በ2018 በጀት አመት ሰፊ ተግባራትን ለመከወን ማቀዱን ጠቁሟል፡፡
ጤና የሁሉም ነገር መሰረተ እንደመሆኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለሚፈጠሩ ሰው ሰራሽ እና ድንገተኛ አደጋዎች የደም እጥረት ሲኖር የሌላ ሰው ደም በመጠቀም የሰዎችን ህይወት መታደግ እንደሚቻል የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡
በአርባምንጭ ከተማ የደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ቡድን አስተባባሪ አቶ በሀይሉ ባሻ፤ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ደም ለጋሽ ማህበራት በባለሙያዎች ሰፊ ርብርብ ደም መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
አቶ በሀይሉ አክለውም፤ ደም ለመለገስ የግንዛቤ ውስንነቶች እንደሚስተዋሉ ተናግረው ይህን ለመቅረፍ በተለያዩ መንገድ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች እየተሰጡ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
በ2017 በጀት አመት 9 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ የታቀደ ቢሆንም 6 ሺህ 378 ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን የገለፁት ደግሞ የአርባምንጭ ደም ባንክ ኃላፊ አቶ ኤርምያስ ባቤና ናቸው፡፡
በበጀት አመቱ 71 ከመቶ አፈፃፀምን ማሳካት ቢቻልም በርካታ ውስንነቶች አፈፃፀሙን ዝቅ እንዲል ምክንያቶች እንደነበሩ ጨምረው አብራርተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ጠንካራ ተግባራትን በማጠናከር ተግዳሮቶችን በመቅረፍና የህብረተሰቡን የግንዛቤ ሁኔታዎች በመጨመር በቀጣይ ሰፊ ስራዎችን ለመስራት የባለድርሻ አካላት ትኩረትና ትብብር ሚናው የላቀ መሆኑን ገልፀዋል ኃላፊው።
በ2018 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ ስምረት አስማማው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የአርባምንጭ ደምና ህብረህዋስ ባንክ በ2017 በጀት አመት ከ6 ሺህ 378 ዩኒት በላይ ደም መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ

More Stories
ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሰራ ነው – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
በሽታ መከላከልንና አክሞ ማዳን ላይ ትኩረት በማድረግ በድንገተኛ ክስተት ለተጎዱ ወገኖች እና ወረርሽኝ ምላሽ የሚሆን 10 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ግብአት ተሰራጭቷል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ
ከደም ተዋፅኦ መድኃኒት በማምረት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገቡ የደም መድኃኒቶችን ለማምረት እየተሰራ ይገኛል – የኢትዮጵያ ደምና ኅብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት