በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ከ36 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ የተሰራው የኡማ ባኬ መንገድ ተጠናቆ ተመረቀ
የመንገዱ መገንባት ለአከባቢው ማህበረስብ ያለው ጠቀሜታ ዘርፈ ብዙ መሆኑም ተመላክቷል ፡፡
በመርሐግብሩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የመንግስት ረዳት ተጠረና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ የመንገድ መሰረተ ልማት የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቶችን ሊደግፍ በሚችል መልኩ ለማስፋፋት መንግስት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
የመንገድ መሠረተ ልማት ልማትን የሚያሳልጡ፣ እድገትን የሚፋጥኑ፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ተስፋን የሚያለመልሙ ሊሆን እንደሚገባ ነው ያነሱት፡፡
በዞኑ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች መኖራቸውን አመልክተው፤ የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የዞኑ ህዝብ እንዲያግዝ ጠይቀዋል ፡፡
የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ልከባቢው ማህበረሰብ የመንገድ መሰረተ ልማት ሁሉን አቀፍና የዘመናት ጥያቄ ምላሽ ነው ብለዋል ፡፡
የአመያ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባሻ በላይነህ አከባቢው ሰፊ የግብርና ምርት ያለበት መሆኑን ጠቅሰው በአከባቢው ምቹ የገበያ ትስስር ለመፍጥር የመንገዱ መገንባት አውንታዊ ሚና ይጫወታል ነው ያሉት ፡፡
ኡማ -ባኬ -ዝጋ መንገድ 12 ኪ.ሜ በላይ ሲሆን 36 ሚለዬን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ፡፡
ዘጋቢ ፡ደረጀ ተፈራ -ከዋካ ቅርነጫፍ

More Stories
የማር ምርት እጅግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጎምቦራ ወረዳ በንብ ማነብ ስራ የተሠማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሰ የግብርና ልማት ላይ አደጋ እንዳያስከትል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የገጠር ኮሪደር ኤኒሼቲቭ የገጠርሪቱን ኢትዮጵያ አኗኗር ዘይቤ በእጅጉ የሚያዘምን መሆኑ ተገለጸ