ሃገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የያዘችውን ውጥን በማሳከቱ ረገድ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራችዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገለጸ

ሃገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የያዘችውን ውጥን በማሳከቱ ረገድ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራችዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሃገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የያዘችውን ውጥን በማሳከቱ ረገድ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ውጤታማ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራችዎች እየተሰሩ መሆኑን የምስራቅ ጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ አስታወቀ።

በዞኑ በ2017 በጀት አመት በቴክኖሎጂ እና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ ላይ ውጤታማ ስራ ስለመሰራቱም ተመላክቷል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አቶ አህመዲን ጀማል ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ የሃገራትን የማደግ ደረጃ ከፍ እያደረገ የመጣውን ቴክኖሎጂ በሃገራችንም ይበልጥ እንዲሰፋ ትኩረት የተሰጠው መሆኑንና እንደ ዞንም ለዘርፉ አጽንኦት ተሰጥቶ በመሰራቱ ውጤት እየተመዘገበ ነው።

በዞኑ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ከመደበኛና ከአጫጭር ስልጠናዎች ባሻገር የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱና አካባቢያዊ አቅሞችን ተጠቅሞ እሴት መጨመር የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠርና በመቅዳት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ተደራሽ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም በዘርፉ ሃገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የያዘችውን ውጥን በማሳከቱ ረገድ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ውጤታማ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች መሰራታቸውን በክልል ብሎም በሃገር አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ወድድሮች ማረጋገጥ እንደተቻለም አብራርተዋል።

በተለይም ቀደም ሲል በውጭ ሃገር ግዢ ተፈጽሞ ይሰራ የነበረን ተንጠልጣይ ድልድይ በቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አማካይነት ተሰርቶ ለዘመናት የቆየውን የማህበረሰቡ ችግር መቅረፍ መቻሉን ያነሱት አቶ አህመዲን፥ ይህም ዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች አሉት ብለዋል።

እንደ ሃላፊው ገለጻ በክልልና በሃገር አቀፍ ወድድር ላይ አሸናፊ የሆነውና አራት ተግባራትን መከወን የሚችለው ቴክኖሎጂ ተጠቃሽ መሆኑን ያወሱት ሃላፊው ሌሎችም በሰልጣኝ ፣ በአሰልጣኝና በኢንተርፕራይዝ ደረጃ የተሰሩ ከ32 በላይ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ማሸጋገር ተችሏል።

ሆኖም ከማህበረሰቡ ፍላጎት አንጻር ቴክኖሎጂ በብዛት ፈጥሮና ቀድቶ ተደራሽ በማደረጉ ረገድ ብዙ መሰራትን እንደሚጠይቅ አመላክተዋል።

በመሆኑም በ2017 በጀት አመት በቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ ኤክሰቴንሽን ዘርፍ ላይ ውጤታማ ስራ ስለመሰራቱም አመላክተዋል።

በካይዘን ፣ በኢንተርፕሪነር፣ በቴክኖሎጂ እና በክህሎት ዘርፍ በየዘርፉ ለተደራጁ አንቀሳቃሾች የተጠናከረ ስልጠና መሰጠቱን የተናገሩት አቶ አህመዲን ይህም ሞዴል ኢንተር ፕራይዞች በመፍጠር ለኢንደስትሪው መጎልበት አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት።

ለነባርና አዳዲስ አንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች ችግሮችን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች በመስጠት እቅዱን መቶ በመቶ ማሳከት እንደተቻለም አቶ አህመዲን ጀማል ከጣቢያችን ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሃገር በቀል እውቀትን ከማልማትና ከማበልጸግ አንጻር ሰፊ ሰራ አንደተሰራ በመጠቆም መሰል ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

ተግበራዊ የጥናትና ምርምር ስራዎች በመስራት የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎች በዘላቂነት ይሰራሉ በማለት በፈጠራ ዘርፍ ለተሰማሩ ሰልጣኞችም ሆኑ አሰልጣኞች እንዲበረታቱ ልዩ ልዩ ድጋፎች እየተደረጉ ስለመሆኑ ገልጸው በዋናነት ችግርን ለመቅረፍ ብሎም ተጠቃሚነትን ለማጎልበት መሰረት ተደርገው የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች የመጠቀም ልምድ ማዳበር ይጠበቅበታል ሲሉም አቶ አህመዲን አስገንዝበዋል ።

ዘጋቢ፡ አማን ቢካ – ወልቂጤ ጣቢያችን