ባለፉት 7 አመታት በአንድ ጀምበር ብቻ ከ7 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በ56 ሚሊዮን የተለያዩ ጠቀሜታዎች ባሏቸዉ ችግኞች መሸፈን መቻላቸዉን የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

ባለፉት 7 አመታት በአንድ ጀምበር ብቻ ከ7 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በ56 ሚሊዮን የተለያዩ ጠቀሜታዎች ባሏቸዉ ችግኞች መሸፈን መቻላቸዉን የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

‎በዛሬዉ ዓለት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በስልጤ ዞን ሁልባረግ ወረዳ በሚገኘዉ ሀጫሞ ቀበሌ ገርባ ተፋሰስ ተካሂዷል።

‎በዘንድሮው የአንድ ጀምበር መርሀ ግብር ላይ በዞኑ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል እየተሰራ ይገኛል።

‎እስከአሁን እየተተከሉ የሚገኙ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ፣ የቡና፣ ቅመማ ቅመም፣ መኖ እና የደን ችግኞች ሲሆኑ የአከባቢን ገጽታን ከመቀየርና ከመጠበቅ ባሻገር ለኢንዱስትሪ ግብኣት ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው፡፡

‎እንደዞን ባለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት ለአረንጓዴ አሻራ ተከላ በተሠጠው ልዩ ትኩረት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በአማካይ 362,500 ለተከላ የደረሰ ሰው በማሳተፍ በተለዩ የተከላ ቦታዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው ከ510,204,338 በላይ ችግኖች 94,925 ሄክታር መሬት መሸፈን ተችሏል፡፡

‎ባለፈው ዓመት የተተከለውን ችግኝ የእንክብካቤ ስራዉን አጠናቀክሮ በማስቀጠል ጽድቀትን በአማካይ 88.81 በመቶ ማድረስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

‎የአረንጓዴ አሻራ ሥራም የዞኑ የደን ሽፋን ወደ 23.2 በመቶ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል፡፡

‎በመርሀ ግብሩ ላይ የተለያዩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ በነቂስ በመዉጣት አሻራቸዉን አኑረዋል።

ዘጋቢ፡ ፍሬህወት ኡሹሌ