የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የአካባቢ ጥበቃን ከማጠናከር ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ አካባቢ ለማውረስ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ
በኮንታ ዞን “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ እንደ ሀገር ለረጅም ዓመታት እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እያስገኘ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምህዳር በመፍጠር ተምሳሌነቷ እያስመሰከረች መሆኗንም አንስተዋል።
የኮንታ ዞን ግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን አስፋው በበኩላቸው በ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በአንድ ጀምበር እንደ ዞን 9 መቶ 72 ሺህ 134 በላይ ሄክታር መሬት ላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተተከለ ይገኛል ብለዋል።
በዞኑ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች ከ57 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ የገለጹት አቶ ፋንታሁን በዛሬው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በተለይም የፍራፍሬ ፣ የቡናና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ባለቸው ችግኞች ላይ ትኩረት መደረጉን አንስተዋል።
አቶ ፋንታሁን አክለውም የዛሬው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ሥራ ለመጪው ጊዜ አሻራና ለነገውም ትውልድ ትልቅ ተስፋ መሆኑን በመረዳት የሚተከሉትን ችግኞች ለውጤት ሊያበቃ የሚችል የእንክብካቤ ሥራ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲደረግበትም ተናግረዋል።
በመርሀ ግብሩ የዞኑ ሁሉም መዋቅር የሥራ ኃላፊዎች፣ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና የአከባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ ራሄል ቡልቻ – ከዋካ ጣቢየችን

More Stories
ባለፉት 7 አመታት በአንድ ጀምበር ብቻ ከ7 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በ56 ሚሊዮን የተለያዩ ጠቀሜታዎች ባሏቸዉ ችግኞች መሸፈን መቻላቸዉን የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል
ዛሬ የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ የነገዋን አረንጓዴ፣ ለምለም፣ የተደላደለችና የበለጸገች ከምባታን የመገንቢያ ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት ነው አሉ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ