በጋዜጣው ሪፖርተር
ተወልደው ያደጉት ከምባታ ዞን አዞዶበኦ በምትባል የገጠር ቀበሌ ነው፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አካል ጉዳተኞች ፌደሬሽን ውስጥ የሒሳብ ሹም ሆነው እያገለገሉ ሲሆን በዱራሜ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ የእንግሊዘኛ መምህር ናቸው፡፡ በመምህርነት ለ26 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ዛሬ ላይ ባለ ትዳር እና የ3 ወንድ ልጆች አባት ሆነዋል፡፡
አቶ ተሾመ እድገታቸው ገጠር ውስጥ ነበር። ልጅነታቸውን ቦርቀው ሳይጠግቡ ድንገት ኩፍኝ የሚባል በሽታ ከቡረቃቸው ገታቸው፡፡ ከ7 እህት ወንድሞቻቸው መካከል ለይቶ ከቤት አስቀራቸው፡፡
እድሜያቸውም ለትምህርት ሲደርስ ታናናሾቻቸው እና የሰፍር እኩዮቻቸው ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ አቶ ተሾመ ግን መግባት አልቻሉም ነበር፡፡ የ4 ዓመት ልጅ እያሉ ነበር የዓይናቸውን ብርሃን ያጡት፡፡
“የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና ልክ የ10 ዓመት ልጅ እያለሁ የትምህርት ዕድል ቀናኝ፡፡ ሻሸመኔ የምትኖር አክስት ነበረችኝ፤ ልትጠይቀን በመጣችበት ሻሸመኔ ዓይነ ስውራን ት/ቤት እንዳለ እና እዛም ገብቼ መማር እንደምችል ለቤተሰቦቼ ነገረቻቸው፡፡ በሰዓቱ ፈረንጆች ወስደው ሊሸጡት ነው በሚል ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡
“አክስቴ ግን እንደ ምንም አግባብታ ሻሸመኔ ካቶሊክ ዓይነ ስውራን ት/ቤት እንድገባ አድርጋኛለች፤ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናዬ ይድረሳት” ብለዋል፡፡
በሻሸመኔ ካቶሊክ ዓይነ ሥውራን ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ትውልድ ቀዬአቸው ተመልሰው ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በከምባታ ዞን በዘና ቤናራ ምሽግዳ መካነ ኢየሱስ ትምህርት ቤት ተምረዋል፡፡
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደግሞ በዱራሜ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረው አጠናቀዋል፡፡ ለዩኒቨርሲቲ የሚያበቃ ውጤት ባያመጡም በሀዋሳ መምህራን ኮሌጅ ተወዳድረው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ለ4 ዓመታት ተከታትለው በዲፕሎማ መርሀ ግብር አጠናቀው መመረቅ ችለዋል፡፡
ሥራ የጀመሩት በአንጋጫ ወረዳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ሆነው ለ5 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ዱራሜ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመልሰው እያስተማሩ ድጋሚ የትምህርት እድል አግኝተው ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በመደበኛ ፕሮግራም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ለ2 ዓመታት ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡
“አካል ጉዳተኛ መሆን በራሱ ተጽዕኖ አለው። ብዙ ችግሮችን ተቋቁሜ አልፌያለሁ፤ በተለይ ትምህርቴን ስማር ከአንዴም ሁለቴ ለህልፈተ ህይወት ተዳርጌ ነበር፡፡” ያሉት አቶ ተሾመ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት 7 ኪሎ ሜትር በእግራቸው ይጓዙ እንደ ነበር ገልፀውልናል፡፡
“ሻሸመኔ ዓይነ ስውራ ትምህርት ቤት ስማር በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ሁሉ ነገሩ ምቹ ነው፤ መጫወቻዎች ጭምር ነበሩት፡፡ ጥሩ ህይወት ነበር ያሳለፍኩት፡፡ ዱራሜ ከመጣሁ በኋላ ግን በጣም ነበር የከበደኝ፡፡
“ከዓይናማዎች ጋር ስለነበር የምማረው ቶሎ ለመግባባት ተቸግሬ ነበር፡፡ እነሱ የሚማሩት በሰሌዳ ነበር፡፡ እኔ ከማዳመጥ ውጭ ምንም አላደርግም ነበር፡፡ ያልገባኝን የምጠይቀው ጓደኛም አልነበረኝም፡፡
“በሂደት ግን እየለመድኩት መጣሁ፡፡ ተማሪዎቹም ክፍል ውስጥ የማደርገውን ተሳትፎ እያዩ ቀስ በቀስ መቅረብ ጀመሩ በማለት” የገጠማቸውን ፈተና አጫውተውናል፡፡
“ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርት ቤቱ ከቤታችን አቅራብያ ስለነበር ብቻዬን እየተመላለስኩ ነበር የተማርኩት፡፡ አንድ መሻገሪያ ወንዝ አለች፤ እሷ ጋር ስደርስ ብቻ እናቴ ትጠብቀኝና ታሻግረኝ ነበር” ብለዋል፡፡
“ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያለው ርቀት ፈታኝ ነበር፡፡ በተለይ እናቴን ዋጋ አስከፍሏታል፡፡ እኔ የደረስኩበትን ደረጃ ለእናቴ ብሰጣት ደስ ባለኝ ነበር” ሲሉ የእናታቸውን ጥንካሬ አድንቀዋል፡፡
“ማለዳ 12 ሰዓት ተነስተን ነበር ወደ ትምህርት ቤት ጉዞ የምንጀምረው፡፡ እናቴ ምርኩዝ ሆናኝ እስከ ክፍል ድረስ ታስገባኝ ነበር፡፡ አስገብታኝም ጥላኝ አትሄድም፡፡ ክፍለ ጊዜውን ጨርሼ እስከ ምወጣ ድረስ ዛፍ ስር ቁጭ ብላ ትጠብቀኝ ነበር፡፡ እናቴ የምትገርም ናት፤ ጎበዝ እናትም ጭምር ናት።
“ለእናቴ ድካም ስል ትምህርቴን ምማረው በሳምንት 3 ቀናትን ብቻ ነበር፡፡ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል እያመላለሰች አስተምራኛለች፡፡ እስካሁንም በህይወት ኖራ የእኔን ስኬት በማየቷ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡” ሲሉ እናታቸው የዋሉላቸውን ውለታ ያወሳሉ፡፡
“ስማር እንግዲህ ቸግሩ በመንገድ ብቻ አላበቃም፡፡ የአመለካከት ችግሩ ደግሞ ይብሳል። ተምሯል የሚባለው ማህበረሰብ ራሱ ብዙ ይቀረዋል፡፡ አንድ ጊዜ የሒሳብ መምህሬ የሒሳብ ፈተና ካልተፈተንክ ብሎ ውጤቴን አበላሽቶብኛል።
“እንደ ሚታወቀው ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ሽምደዳ ነክ ትምህርቶችን እንጂ የሒሳብ ትምህርት አንማርም፡፡ ታድያ ይህ መምህር ላስረደው ብሞክርም ጆሮ አልሰጠኝም ነበር፡፡ በሌሎች መምህራን ልመና ነው ወጤቴን ያስተካከለልኝ፡፡ ማህበረሰቡ ዘንድ አመለካከቱ ገና አልተቀረፈም” ሲሉ ኮንነዋል፡፡
በተመሳሳይ ከክፍል ተማሪዎቻቸው የገጠማቸውን ሲያነሱ የሚፅፉበት የብሬል ወረቀት ብርቅ ሆኖባቸው ልክ መፃፍ ሲጀምሩ ተማሪዎቹ ይከቧቸው እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡
ሌላኛውን ገጠመኛቸውን ያነሳሉ፡- “ታላቅ ወንድሜ የእናቴን ድካም ለመቀነስ ‘ዛሬ እኔ አደርሰዋለሁ’ ብሎ እንደሚመልሰኝም ጭምር ነግሯት ትምህርት ቤት አደረሰኝ፡፡ ረስቶ ሳይመልሰኝ የጥዋት ፈረቃ ነበርኩ የከሰዓት ፈረቃ ደረሰ፡፡
“ብዙ ከጠበኩት በኋላ ሲርበኝ ተስፋ ቆርጬ ጥበቃውን ዱላ ነገር ስጠኝ ብዬ ወጥቼ ሄድኩኝ። የሆነ አካባቢ ስደርስ 2 ሜትር ርቀት ያለው ጉድጓድ ጫፍ ላይ ስደርስ ከርቀት ‘ወደ ቀኝ ወደ ቀኝ ‘የሚል ድምፅ ሰማሁ፤ ወደ ቀኝ ስዞር ጉድጓድ ውስጥ ገባሁ፡፡ ላካ ሰውየው የራሱን ቀኝ እንጂ የኔን ቀኝ አላስተዋለም ነበር፡፡ ፈጣሪ ጠብቆኝ ምንም ሳልጎዳ ተርፌያለሁ፡፡”
በሥራ የገጠማቸውን ደግሞ ይቀጥላሉ፡-
“አስተምሬ ወደ ቤት ስሄድ ከርቀት በቅሎ ሣር ሲግጥ ድምፅ ይሰማኝ ነበር፡፡ እየቀረብኩ ስመጣ ግን ድምፁ ጠፋ፡፡ አጠገቡ ደርሼ በቅሎው እላዬ ላይ ሊወጣ ሲል ከርቀት ሰዎች አይተው ደርሰው ያስጣሉኝ ጊዜም ነበር፡፡”
“እናቴ ሁልጊዜ ጥላ ሥር ኩርምት ብላ መቀመጧን እና የኔን የትምህርት ፍላጎት ያየ የታሪክ መምህሬ ነበር፤ ሙሉጌታ ዛራ ይባላል፡፡ የትምህርት ቤቱን ርዕሰ መምህር ጨምሮ ሁሉንም መምህራንን አስተባብሮ በየወሩ የቤት ኪራይ ችለውኝ ከተማ እንድማር አድርገውኛል፡፡
“በሰዓቱ በባዶ እግሬ ነበር የምማረው፡፡ ልብስም፤ ምግብም ይቸግረኝ ነበር፡፡ ሁሉንም ነገር አመቻችተውልኝ ትምህርቴን በአግባቡ አንድም ቀን ሳልቀር እከታተል ነበር፡፡ እናም የመጀመሪያ ጊዜ 120 ብር ሰብስበው የሰጡኝን ቀን መቼም አረሳውም፤ በጣም ነበር ደስ ያለኝ” ሲሉ ደስ የተሰኙበትን ቀን ያወሳሉ፡፡
“እንግዲ ከብዙ እንግለት በኋላ ራሴን ችዬ መኖር ስጀምር ቀርበውኝ የማያውቁ ሰዎች ሁሉ ይቀርቡኝ ጀመር፡፡ አነድ ያጎቴ ልጅ አብራኝ ትኖር ነበር፡፡ ጓደኛዋ ብዙ ጊዜ ወደ ቤት ስትመጣ አስተዋውቃኝ ነበር፡፡
“የአጎቴ ልጅ ስታገባ የሠርጓ ዕለት እኔ ስላገበሁ አንተም ማግባት አለብህ፤ ስለዚህ ጓደኛዬን አግባት አለችኝ፡፡ እኔም የጋብቻ ጥያቄ አቀርብኩላት፡፡ እሷ ብትስማማም ቤተሰቦቿ ግን ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡
“እንዴት እንደዚህ ዓይነት ሰው ታገቢያለሽ ብለው አምቧ ጓሮ ፈጥረው ነበር፡፡ ለማሳመን ብትሞክርም አሻፈረኛ አሉ፡፡ በመጨረሻም በራሳችን ለመጋባት ወሰንን፡፡ በምን ዓይነት መንገድ እንደምንጋባ አውጥተን እያወረድን ሳለን አንድ ቀን በሬዲዮ ስለ የሺህ ጋብቻ ማስታወቂያ ሰማሁ፡፡ ስልክ ቁጥር ሲያስተላልፉ ይዤ ወድያው ደወልኩኝ፡፡ ስልኩን ያነሳው ልጅ አድራሻዬን ስነግረው አወቀኝ፡፡ አጋጣሚ ሆኖ አብሬው የተማርኩት ልጅ ነበር፡፡
“ልጁ አስመዝግቦኝ ያለ ምንም ወጪ ፈጣሪ ደግሶልን ፕሮግራሙ ጊዮን ሆቴል ተዘጋጅቶ ህዳር 8/2005 ዓ.ም ተጋባን፡፡” ሲሉ ወደ ትዳር ዓለም የገቡበትን አጋጣሚ አጫውተውናል፡፡
“አካል ጉዳተኞች ስነ-ልቦናቸውን አጠናክረው ራሳቸውን ማበርታት አለባቸው፡፡ ያንን ደግሞ የሚያደርጉት አሁን ላይ ዘመናችን በቴክኖሎጂ እያደገች ስለሆነ በማንኛውም አቅጣጫ ራሳቸውን ማብቃት አለባቸው፡፡
“በተለይ አይነ ስውራን ከዚህ በፊት ሰው ነበር የሚያነብልን፡፡ አሁን ላይ ግን ዓለም በቴክኖሎጂ በማደጓ ሁሉ ነገር ተመቻችቷል፡፡ ስለዚህ ዓለምን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
“ለዚህ ደረጃ ያበቃችኝ እናቴ ስለሆነች እናቴን በጣም አመሠግናለሁ፤ እንዲሁም ደግሞ የእናቴን ሸክም ያቀለለልኝ መምህር ሙሉጌታን እና አጠቃላይ የዱራሜ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን አመሠግናለሁ፡፡” ሲሉ በሕይወታቸው አዎንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉትን ሰዎች አመስግነዋል፡፡
“እኔ የደረስኩበትን ደረጃ ለእናቴ ብሰጣት ደስ ባለኝ ነበር” – መምህር ተሾመ አንሼቦ

More Stories
“ትልቁ ካፒታል ታማኝነትን ማትረፍ ነው” – ዶክተር ኃይሉ ታምራት
“የሰው ፍቅርን አትርፌበታለሁ” – መምህር ሰለሞን ወርቅነህ
“ችግር ተስፋ ቢስ ሊያደርገኝ ሞከረ፤ እድል ግን አልሰጠሁትም” – ወጣት መውደድ ታደሰ