በ2018 በጀት ዓመት የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል – አቶ ፍቅሬ አማን
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2018 በጀት ዓመት የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የክልሉ የመንግስት ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ የሚቀርብበት መድረክ በታርጫ ከተማ “ማንሰራራት ለክልላችን ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።
ክልላዊ አንድነትንና ህብረብሔራዊ ተግባቦትን ለማስረጽ በተሠራው ሥራ አመራሩ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆኑን አቶ ፍቅሬ አማን ገልጸዋል።
በመደበኛ የፓርቲ ተግባራት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጠናከር በክልሉ ያለውን ጸጋ በአግባቡ በመጠቀም አሁንም በልዩ ትጋትና ቁርጠኝነት ይሠራል ብለዋል።
የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የተጀመሩ መሶብ አንድ ማዕከል ግንባታ ሥራዎች በክልሉ ሁሉም ዞኖች ገቢራዊ ስለመሆናቸው በመግለጽ በ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚሆንም በአጽንኦት ገልጸዋል።
የፓርቲና የመንግስት ኢኒሼቲቮችን ማሣካት፣ የተቋም ግንባታ ማከናወን፣ አሰራርን ማናበብ እንዲሁም የቴክኖጂ ማላመድ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፤ የዘንድሮው ማጠቃለያ ጉባኤ በፓርቲው መሪነት የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ውጤት የተመዘገበባቸው ናቸው ብለዋል።
በህዝቦች ነጻ ፍቃድ በመመካከር ሀገርን ለማጽናት ሀገራዊ ምክክር እየተካሄደ ባለበት ወቅት እየተካሄደ ያለ ጉባኤ መሆኑ ለየት እንደሚያደርገውም ጠቅሰዋል።
በፓርቲው መሪነት የተጀመሩ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራትን በማከናወን በድል የተጠናቀቀ በጀት ዓመት ነበር ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አዲስዓለም ታዬ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)