ፒኤስጂ ፌራን ቶሬስን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ!

ፒኤስጂ ፌራን ቶሬስን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ!

የፈረንሳዩ ክለብ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን የፊት መስመር ማጥቃት ሃይሉን የበለጠ ለማጠናከር አልሞ ፌራን ቶሬስን ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በይፋ ማስፈረሙን አሳውቋል።

የፓሪሱ ክለብ የ 26 ዓመቱን አጥቂ ዝውውር ለማጠናቀቅ 50 ሚሊዮን ዩሮ የከፈለ ሲሆን፣ ተጫዋቹ በፓርክ ዴ ፕሪንስ እ.ኤ.አ እስከ 2031 ድረስ የሚያቆየውን የ 5 ዓመት ኮንትራት ተፈራርሟል።

ፌራን ቶሬስ በፒኤስጂ ቀደም ሲል በፖርቱጋላዊው አጥቂ ጎንዛሎ ራሞስ ይለበስ የነበረውን ታሪካዊውን የ9 ቁጥር ማልያ በመረከብ ለአዲሱ ክለቡ ግልጋሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል።

ቶሬስ በስፔን ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በነበረበት የክለብ ቆይታ ሁለገብ የማጥቃት ብቃቱንና ግብ የማግባት ጥበቡን አሳይቷል።

ቶሬስ ወደ ፓሪስ ማምራቱን ተከተሎ በሰጠው አስተያየት”እንደ ፒኤስጂ ያለ ታላቅ ታሪክ እና ትልቅ አላማ ያለው ክለብን በመቀላቀሌ እጅግ ኮርቻለሁ፤ ከአዲሶቹ የቡድን አጋሮቼ ጋር ለመጫወትና አዳዲስ ዋንጫዎችን ለማንሳት ጉጉት አድሮብኛል” ብሏል።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ