የክልሉ መንግስት ያወጣቸው የፋይናንስ አስተዳደር አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ተፈጻሚ በማድረግ ላይ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚያስፈልግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ገለጸ
ሀዋሳ፣ ሰኔ 06/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉ መንግስት ያወጣቸው የፋይናንስ አስተዳደር አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ተፈጻሚ በማድረግ በሒሳብ አያያዝ፣ በግዢና ንብረት አስተዳደር ላይ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚያስፈልግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ገልጿል።
ቢሮው ለአየር ንብረት ለውጥና መሬት አስተዳደር ፕሮግራም አስተባባሪዎች፣ ለወረዳ ፋይናንስ ፎካሎች፣ ለግዢ ባለሙያዎች እና ለህብረት ስራ ኦዲተሮች 2ኛ ዙር ሥልጠና በወልቂጤ ከተማ እየሰጠ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በመንግስት ፋይናንስ ዘርፍ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ኑራሙ እንዳሉት የአየር ንብረት ለውጥና መሬት አስተዳደር ፕሮግራም በአለም ባንክና በፌደራል መንግስት የበጀት ድጋፍ የሚተገበር ፕሮግራም ሲሆን በአየር ንብረት ለውጥና መሬት አስተዳደር ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ፕሮግራም ነው።
የፕሮግራሙ የፋይናንስ አጠቃቀምና አስተዳደር ሥርዓት የመንግስትን የሒሳብና የበጀት አስተዳደር ሥርዓትን በተከተለ መልኩ መፈጸም እንዳለበት የተናገሩት አቶ ታረቀኝ ሥልጠናው የሒሳብ፣ የግዢና የኦዲተር ባለሙያዎች የክልሉ መንግስት ያወጣቸው የፋይናንስ አስተዳደር አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ተፈጻሚ በማድረግ በኩል ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት እንደሚረዳ ገልጸዋል።
በዚሁ በሁለተኛው ዙር ሥልጠና ከስልጤ፣ ከሀዲያና ከከምባታ ዞኖች የተወጣጡ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ፣ ተረፈ ሀብቴ ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የጂንካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የተጠርጣሪ ማቆያና የቢሮ ህንጻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው በተገኙበት በደማቅ ሥነ ስርዓት በይፋ ተመረቀ
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ1 ቢሊዮን 4 መቶ 21 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ
በትራንስፕርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እየተደረገ ባለው ከታሪፍ በላይ ጭማሪ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች እየተጋለጥን ነው ሲሉ በወልቂጤ ከተማ መናኽሪያ አግኝተን ያነጋገርናቸው ተሳፋሪዎች ተናገሩ