የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዕቅድ ዙሪያ በታርጫ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው
የጽህፈት ቤቱ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ነጋ አበራ፤ በዘርፉ በ2018 በጀት ዓመት የተገኙ ድሎችን በማጠናከር በ2019 በጀት አመት የክልሉን ህዝብ ሁሉ አቀፍ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።
ፓርቲው በክልሉ ባለፉት አመታት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን የጠቀሱት አቶ ነጋ አበራ፤ በ2019 በጀት አመት ህዝቡ በምርጫ ካርዱ የሰጠውን አደራ እና እንደ ብልፅግና ፓርቲ የተገባውን ቃል ለመፈፀም በላቀ ቁርጠኛነት እንደሚሰራም አብራርተዋል።
በመድረኩ የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ የ2018 በጀት ዓመት በጠንካራ አደረጃጀት በርካታ ድሎችና ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚሁ ስኬት ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት በመትከል በአባላትና በአመራር መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት መፍጠር መቻሉን አንስተዋል።
የቤተሰብ እና የኅብረት አደረጃጀቶች በሁለንተናዊ መስክ አርአያ የሆኑ አመራር እና አባላትን በማፍራትና በማጠናከር በክልሉ የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማሳካት የአደረጃጀት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አመላክተዋል።
በተለይም የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መንትያ ግቦችን በተደራጀና በተቀናጀ አሰራር በመምራት ብልጽግና ፓርቲ ምርጫውን በአብላጫ ድምጽ እንዲቀዳጅ የአደረጃጀት መሪነት ሚና የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ አዲስአለም ታዩ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ኦሞ ባንክ ሳውላ ዲስትሪክት በ2018 በጀት ዓመት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ቁጠባ ማስመዝገቡን ገለጸ
እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
በግብርናው ዘርፍ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመረጃ ጥራት ዙሪያ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ