በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሠማሩ የግል ባለሀብቶች ከመንግስት የተረኩቡትን ሀብት በተገቢው እንዲያለሙ ተጠየቀ
የኣሪ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ “ኢንቨስትመንት ለላቀ ብልጽግና” በሚል መርህ በዞኑ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ከተሰማሩ የግል ባለሀብቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የኣሪ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅረስላሰ ጀማል በመድረኩ እንደገለፁት፤ በዞኑ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ 77 የግል ባለሀብቶች ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል እያንቀሳቀሱ ይገኛል።
በዞኑ ለኢንቨስትመንት ከተላለፉ መሬቶች 36 በመቶ ብቻ እየለማ እንዳለ ገልፀው፤ በዘርፉ የሚሰተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ዞኑ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢንቨስትመንት ለሀገር ግንባታና ብልጽግና ካለው የላቀ አስተዋጾ አንጻር በዞኑ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
በዞኑ ለኢንቨስትመንት በሚቀርቡ መሬቶች ላይ የሚሰተዋሉ የግንዛቤና አፈፃፀም ችግሮችን በዘላቅነት በመፍታት ዘርፉን ለማሳደግና የዞኑንም ጥቅም ለማሳደግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አፀደ አይዛ፤ መንግስት የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማዘመን የሪፎርም እና በርካታ የአሰራር ማሻሸያዎችን ማድረጉን አብራርተው፤ በተዋረድ ያሉ የመንግስት መዋቅሮችና በዘርፉ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች የተፈጠሮ ዕድሎችን መጠቀም አለባቸው ብለዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለው በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት እንደሚሰራ አረጋግጠው፤ አልሚ የግል ባለሀብቱም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ማህበረሰቡን ከቱርካና ሐይቅና ከኦሞ ወንዝ ሙላት ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በስፍራው በመገኘት ተመለከቱ
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በየደረጃዉ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ አስታወቀ
የህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ያሳኩት የጋራ ድል መሆኑን የጨታ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ