በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ ለ2መቶ 50 ድጋፍ ለሚሹ አቅመ-ደካማና አረጋውያን ማዕድ የማጋራት መርሃ-ግብር ተደረገ
የ1ሺ 4መቶ 46ኛውን የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ2መቶ 50 ድጋፍ ለሚሹ አቅመ-ደካማና አረጋውያን ከ5መቶ 70 ሺ በላይ በሆነ ወጪ ማዕድ የማጋራት መርሃ-ግብር ተደረገ ፡፡
በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ አስተዳደር ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት የአደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና እንዲሁም ከወረዳው ሰራተኛና ማህበራዊ ተቋም ጋር በመሆን የ1ሺ 4መቶ 46ኛውን የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ ከሁሉም የወረዳው ቀበሌዎች ለተውጣጡ 2መቶ 50 ድጋፍ ለሚሹ አቅመ-ደካማና አረጋውያን 5መቶ 70 ሺ 5መቶ ብር በሆነ ወጪ ማዕድ የማጋራት መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡
የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ተሚማ ሙዴ መረዳዳት እና መደጋገፍ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን ሞራላዊ ግዴታም ጭምር እንደሆነ አንስተው የመረዳዳት ባህሉና ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የማዕዱ ተጋሪዎች በበኩላቸው ለተደረገላቸው መልካም ተግባር ምስጋና አቅርበዋል ።
ምንጭ ፡ የሳንኩራ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን
More Stories
የወረዳው ሴቶች አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ገለጹ
በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ መሃል የሚገኘው የአስፓልት መንገድ በመበላሸቱ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ
የአርሶ አደሩን የምርጥ ዘር ፍላጎት በክልሉ የመልማት አቅም ብቻ ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ