በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ባደዋቾ ክላስተር በ2017/18 በበልግ የእርሻ ወቅት በክላስተር የተዘራ የበቆሎ ማሳ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በተመራ ልኡክ የመስክ ምልከታ ተደረገ
በምልከታው ከበቆሎ ማሳ በተጨማሪ በአካባቢው የተከናወኑ የተቀናጀ የግበርና ሥራ እንቅስቃሴ በዞኑና በወረዳዎቹ አመራሮች እንዲሁም በባለሙያዎች ተጎብኝቷል።
በሀዲያ ዞን ምስራቅ ባደዋቾ ወረዳ በ2017/18 የምርት ዘመን በበልግ አርሻ ወቅት በዘር ከተሸፈነው 7 ሺህ 2 መቶ ሄክታር ማሳ ውስጥ 5 ሺህ 9 መቶ 86 ያህሉ በኩታ ገጠም የተዘራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በወረዳው 99 ክላስተር ማሳ በዘር ከተሸፈነው የአቶቴና ሊቻ ክላስተሮች ምልከታ የተደረጉ ሲሆን ከሄክታር 60 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: ኤልያስ ኤርሶ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል