በክትባት ዘመቻው 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ህፃናትን ይከተባሉ-የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ
ከግንቦት 22/2017ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ለሚካሄደው የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ጠይቋል።
ከግንቦት 22 እስከ 25/2017ዓ.ም በሚካሄደው ዘመቻ 1ሚሊዮን 4መቶ ሺህ ህፃናትን ተደራሽ እንደምደረግ ቢሮው አስታወቀ።
በክልሉ ኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ ባይጽማል ቀበሌ ዞናዊ የማስጀመሪያ መረሐ ግብር ላይ ተገኝተው ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የዘርፈ ብዙ ኤች.አይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍና ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ጋርሾ በበጀት አመቱ በክልሉ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የተሳካ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ፡፡
በክልሉ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ክትባት ዘመቻ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ህፃናት ይከተባሉ ብለዋል ፡፡
ከፖሊዮ ክትባት ጎን ለጎን በወባ በሸታ መከላከያና ምልክቶች ላይ በተቀናጀ መንገድ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ያመላከቱት አቶ ማቴዎስ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና መከተብ ያለባቸውን ህፃናት በሙሉ እንዲያስከትቡ አሳስበዋል።
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ይሁን ገሎ በማስጀመሪያው ባስተላለፉት መልዕክት
በዞኑ በተያዘው የሁለተኛ ዙር ክትባት ዘመቻ 77 ሺህ 3መቶ 6 ህፃናት ክትባት ያገኛሉ ነው ያሉት ፡፡
ዘጋቢ ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ-ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የጡት ካንሰር ተገቢው ህክምና በወቅቱ ካልተደረገ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ እንደመሆኑ ድንገት ሲያጋጥም በባህል ህክምና ከመዘናጋት ይልቅ በአፋጠኝ ወደ ጤና ተቋማት መሄድ ተገቢ ነው – ዶክተር ተሾመ አለምቦ
ህብረተሰቡ በሽታን ለመከላከል የሚሰጡ ክትባቶችን በአግባቡ በመውሰድ እንዳለበት ተገለጸ
የመስቀል በዓል አከባበር ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው