የታርጫ አጠቃላይ ሆስፒታል ለተገልጋዮች የተሻለ የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀ
ሆስፒታሉ አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ ተገልጋዮች እንዳይጉላሉ ለማስቻል በየደረጃው ከሚገኙ ባለሙያዎችና የባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሠራ እንዳለም ተገልጿል።
ሆስፒታሉ በመድኃኒት አቅርቦት የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በበጀት ዓመቱ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሕዝብ መድኃኒት ቤት ተከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በታርጫ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ2 መቶ 40 በላይ በተለያዩ ደረጃ የሰለጠኑ የሕክምና ባለሙያዎችና ከ1 መቶ 30 በላይ የአስተዳደር ሠራተኞች አገልግሎቱን እየሰጡ መሆናቸውን ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ከታርጫ ከተማ የሕክምና አገልግሎት ሊያገኙ የመጡ አቶ ቶማስ ቡናሮ፣ ወይዘሮ አልማዝ ተክሌና አቶ ናግሻው በሰጡን አስተያየት ምንም ሳይጉላሉ የሕክምና አገልግሎት ሳይቋረጥ መታከም መቻላቸውን ተናግሯል ፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ጥሩ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አብራርተዋል ።
በሆስፒታሉ አልፎ አልፎ የሚታየው የመድኃኒት እጥረት እንዲቀረፍ የሚያስችል ተግባር እንዲከናወንም ጠይቀዋል።
አሁን ላይ በሁሉም የሕክምና አሰጣጥ ሂደት ደስተኞች እንደሆኑም ተገልጋዮች አረጋግጠዋል።
የታርጫ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ሌንጮ በበኩላቸው ከሆስፒታሉ ባለሙያዎች ጋር በተቀናጀ ጥረት የአገልግሎት አሰጣጡ በተሻለ ሁኔታ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከዞኑና ከአጎራባች አካባቢዎች አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሳይጉላሉ ታክመው እንዲመለሱ ለማስቻል ባለሙያዎች እያደረጉ የሚገኙት ጥረት የሚደነቅ እንደሆነም ነው የገለጹት።
ዘጋቢ ፡ አድስአለም ታዩ -ከዋካ ቅርንጫፍ
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ሊካሄድ ነው
የተቀናጀ ኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህጻናትን ተደራሽ ይደረጋል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ
የሣንባ በሽታንና ሌሎች ስር የሰደዱ የመተንፈሻ አካላት ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ