በመንግስት የሚገነቡ ልማቶችን የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች ጎበኙ

በመንግስት የሚገነቡ ልማቶችን የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች ጎበኙ

ሀዋሳ፡ ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በፌደራል መንግስት የሚገነቡ መሠረተ ልማቶችን የቤንች ሸኮ ዞን የጤና ባለሙያዎች እና ስራተኞች ተዘዋውረው ጎብኘተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት በአካባቢው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የዞኑ ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደረጉ ናቸው ብለዋል።

በዞኑ ከሚገኙ ከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች የተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ያደረጉት በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የደንቢ ሎጅ ሲሆን፥ የሎጁ ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጋሻው ዳዊት እንደገለፁት፥ ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታስቦ እየተገነባ መሆኑን አስታውሰው፥ ፕሮጀክቱን በየጊዜው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መጎብኘታቸው ተጨማሪ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 96 በመቶ መድረሱን አመላክተው ከግባታው ጀምሮ ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠረ ቢሆንም፥ ነገር ግን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአካባቢው ገፅታ ከመለወጡ ባሻገር ተጨማሪ የስራ እድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል።

ሌላው የጉብኝቱ አካል የነበረው በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት የሚዛን አማን አለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሲሆን የፕሮጀክቱ የሳይት መሀንዲስ ኢንጅነር ጋሻው ድረስ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ወደ 78 በመቶ መድረሱን ገልፀዋል።

አጠቃላይ አስፓልት ከሚለብሰው 2 ነጥብ ሶስት ኪሎ ሜትር የአስፓልት ንጣፍ ስራ ውስጥ አስከ አሁን ሶስት መቶ ሜትር የአስፓልት የማንጠፍ ስራ መከናውኑንና ገልፀው የአካባቢው ማህበረሰብ የሚያደረገው እገዛ ስራውን እንድናፋጥን አቅም ፈጥሮልናል ብለው።

የሁለቱም ፕሮጀክቶች ግንባታ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የዞኑም ሆነ ሌሎች አመራሮች እገዛና ድጋፍ የራሡን እግዛ ማበረከቱን የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ተናገረዋል።

ፕሮጀክቶቹን ከጎበኙት የጤና ባለሙያዎች መካከል ፍሬህይወት ፍቅሩ እና ግርማዬ ቬርሙስ እንደተናገሩት ልማቱ የአካባቢውን ገፅታ ከመቀየሩ ባሻገር የኢኮኖሚ አቅምም ይፈጥራል ብለዋል።

ከለውጡ ባኋላ በዞኑ እየተከነወኑ ያለው ልማቶች ለአካባቢ እምቅ አቅም እንዳለው ማሣያ ነውም ብለዋል።

ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ አሳሳኸኝ – ከሚዛን ጣቢያችን