ማንቸስተር ሲቲ በኖቲንግሃም ፎረስት ተሸነፈ

ማንቸስተር ሲቲ በኖቲንግሃም ፎረስት ተሸነፈ

በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ ሻምፒዮኑ ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ በኖቲንግሃም ፎረስት 1ለ0 ተሸንፏል።

የኖቲንግሃም ፎረስትን የማሸነፊያ ግብ ሆድሶን ኦዶዬ በ83ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

ኖቲንግሃም ፎረስት ማንቸስተር ሲቲን ሲያሸንፍ ከ9 ጨዋታዎች በኋላ ነው።

ለመጨረሻ ጊዜ ሲቲዝኖቹን የረቱት እንደ አውሮፓውያኑ በ1997 ነበር።

በአሰልጣኝ ኑኖ ስፒሪቶ ሳንቶ የሚመራው ኖቲንግሃም ፎረስት ማሸነፉን ተክሎ ነጥቡን 51 በማድረስ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ማንቸስተር ሲቲ በአራት ነጥብ አንሶ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ፕሪሚዬርሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከሳውዝሃምተን፣ብራይተን ከፉልሃም እንዲሁም ክርስቲያል ፓላስ ከኢፕሲች ታውን ይጫወታሉ።

ብሬንትፎርድ ከአስቶንቪላ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ሲጫወቱ ዎልቭስ ከኤቨርተን ደግሞ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሚገናኙ ይሆናል።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ