የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘውን ብሉ ኤለፋንት ፋይበር ቦርድ ካምፓኒ ጎበኙ
የቻይና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የሆነው ይህ ድርጅት ኤም.ዲ.ኤፍና ኤች.ዲ.ኤፍ አምራችና 5.1 ቢሊዮን ካፒታል የሚያንቀሳቅስ ነው።
ፕሮጀክቱ 369 ቋሚና በግንባታ ሂደት ላይ ከ5000 በላይ ሰራተኞችን ይዟል።
የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የሆነው ካምፓኒው የውጭ ምርቶችን የሚተካ እንዲሁም ወደ ውጭ ምርቶችን የሚልክ ድርጅት ነው።
የግንባታ ሂደቱ አሁን ላይ ከ75 በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን በአመቱ መጨረሻ ወደ ሙሉ የማምረት አቅም ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እና የኢፌዲሪ ኢንዱስትሪ ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴውን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ