በዩሮፓ ሊጉ እና ኮንፍረንስ ሊጉም የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መካሄድ ይጀምራሉ
ሀዋሳ፡ የካቲት 27/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዩሮፓ ሊጉ ወደ ሩብ ፍፃሜው ለማለፍ የሚካሄዱት የመጀመሪያው ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መካሄድ ሲጀምሩ ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ስፔን አቅንቶ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር 2 ሰዓት ከ45 ላይ የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።
በሪያል አሬና ስታዲየም በሚካሄደው ጨዋታ በቀያይ ሰይጣኖች በኩል ማኑኤል ኡጋርቴ እና ሀሪ ማጓር ወደ ስፔን ባቀናው የማንቸስተር ዩናይትድ ስብስብ ውስጥ አለመካተታቸው ተገልጿል።
18 ተጫዋቾችን ይዘው ያቀኑት አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም የዩሮፓ ሊግን ማሸነፍ መቻል በዩናይትድ ሁሉንም ነገሮች የመቀየር ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ሌላኛው የእንግሊዙ ክለብ ቶትንሃም ወደ ሆላንድ አቅንቶ ከኤዜድ አልካማር ጋር ይፋለማል።
እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት ላይ ሮማ ከአትሌቲክ ቢልባኦ፣ አያክስ ከኢንትራክት ፍራንክፈርት እና ቪክቶሪያ ፕሌዘን ከላዚዮ የሚያደርጉት ተጠቃሽ ጨዋታዎች ናቸው።
በኮንፍረንስ ሊጉ ደግሞ ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ከኮበንሀቨን ጋር ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታል።
ኮል ፓልመር የዴንማርኩን ክለብ በሚገጥመው የቼልሲ ስብስብ መካተቱ ተነግሯል።
በዚህም በኮንፍረንስ ሊጉ በምድብ ማጣሪያው ከስብስቡ ውጪ ተደርጎ የነበረው ኮል ፓልመር በኮንፍረንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች