የቅርጫት ኳስ ሻምፒዮናው እንደቀጠለ ነው
ከፍተኛ ፉክክር እየተደረገበት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ስፖርት 3ኛ ዙር ሀገር አቀፍ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የሴቶች ጨዋታዎች ዛሬ መቋጫውን አግኝቷል።
በትላንት ውሎ ሁለት ጨዋታን የተደረገ ሲሆን ወልቂጤ ከተማ ከባህርዳር ያገናኘው ጨዋታ በወልቂጤ ከተማ 56 ለ46 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል።
በሁለተኛው መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ሲጫወቱ ሀዋሳ ከተማ 64 ለ47 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስተኛውን ዙር በድል ማጠናቀቅ ችሏል።
ውድድሩ ዛሬም በሶስት ጨዋታዎች የሚቀጥል ሲሆን በመጀመሪያው መርሀግብር ኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ከ ፋሲል ከተማ ጋር ረፋድ ላይ ይጫወታሉ።
የእለቱ ሁለተኛ መርሀግብር ሸገር ከተማ ከወልቂጤ ከተማ የሚያገናኝ ይሆናል።
የእለቱ የመጨረሻ መርሐግብር በጋምቤላ ከተማና በሀዋሳ ከተማ መካከል ቀን 6:00 ሰአት ላይ የሚደረግ ይሆናል።
ዘጋቢ : ዳዊት ዳበራ-ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች