ሀዋሳ ከተማ መቀሌ 70 እንድርታን በመርታት በሰፊ የግብ ልዩነት በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬርሊግ ሀዋሳ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን 5ለ2 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለሀዋሳ ከተማ የማሸነፊያ ግቦችን አሊ ሱሌማን 3 ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ሲችል ቢንያም በላይ እና አቤኔዘር ዮሐንስ ቀሪ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል።
መቀሌ 70 እንድርታን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦችን ያሬድ ብርሐኑ በፍጹም ቅጣት እና ቦና አሊ አስቆጥረዋል።
አሊ ሱሌማን ዘንድሮ በፕሪሚዬርሊጉ ከባህርዳር ከተማው አጥቂ ወንድወሰን በለጠ በመቀጠል ሀትሪክ 2ኛው ተጫዋች ሆኗል።
ሀዋሳ ከተማን በድጋሚ በአሰልጣኝነት የተረከበው ሙሉጌታ ምህረት የመጀመሪያ የፕሪሚዬርሊግ ድሉን አስመዝግቧል።
ሀዋሳ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ በ19 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
3ኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንድርታ በበኩሉ በ22 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ፡ በሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች