በእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ 5 ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ
የ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ በሳምንቱ አጋማሽ ዛሬም መከናወኑን ሲቀጥል 5 ተጠባቂ ጨዋታዎች ምሽት ላይ ይካሄዳሉ።
ምሽቱን ከሚከናወኑ ጨዋታዎች መካከል የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከኒውካስል፣ ቶትንሃም ከማንቸስተር ሲቲ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከአርሰናል የሚገናኙበት መርሐግብሮች የተሻለ ግምት አግኝተዋል።
የፕሪሚዬርሊጉ የዋንጫ አሸናፊነቱን ለማረጋገጥ በመንደርደር ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል ይበልጥ በተከታዮች ጫና ማሳደር ያስችለው ዘንድ በዕጅጉ የሚያግዘውን ወሳኝ መርሐግብር ምሽት 5 ሰዓት ከ15 በአንፊልድ ከኒውካስል ጋር ያከናውናል።
የመርሲሳይዱ ክለብ በሜዳው በሁሉም ውድድሮች ባለፉት 17 ተከታታይ ጨዋታዎች ቢያንስ 2 እና ከዚያ በላይ ጎል በማስቆጠር ስኬታማ የሚባል አፈፃፀም አስመልክቶናል።
በምሽቱ ዘንድሮ በሁሉም ውድድሮች 51ኛ የጎል ተሳትፎውን ማድረግ የቻለው ሞሐመድ ሳላህ እና ለኒውካስል በ76 የፕሪሚዬርሊግ ጨዋታዎች 50ኛ ጎሉን ባለፈው ሳምንት ማስቆጠር የቻለው አሌክሳንደር አይሳክ ትኩረትን የሚስቡ ተጫዋቾች ናቸው።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ቶትንሃም ከማንቸስተር ሲቲ ሌላኛውን ተጠባቂ ጨዋታ ያካሂዳሉ።
ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስሊግ ተሳትፎ ደረጃን ለማግኘት ወሳኝ ፍልሚያ ይጠብቀዋል።
በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ደግሞ በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ እና 3ኛ ላይ የሚገኙት አርሰናል ይፋለማሉ።
በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ከኢፕሲች ታውን፣ ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን ይጫወታሉ።
ትናንት ምሽት በተካሄዱ ጨዋታዎች ቼልሲ ሳውዝሃምተንን 4ለ0 በመርታት ከ3 ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት መመለሱ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች