የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ደንብ መርምሮ አጸደቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ደንብ መርምሮ አጸደቀ

ሀዋሳ፡ የካቲት 13/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን መንግስት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን በወጣ ደንብ ላይ በዝርዝር መክሮ አጽድቋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬ ውሎ የክልሉን መንግስት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን በወጣ ደንብ ዙሪያ በዝርዝር መክሯል።

በክልሉ ፍርድ ቤቶች ለሚሰጥ የዳኝነት አገልግሎት ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ ለማስከፈልና የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን፣ እንዲሁም የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት በማይገድብ ሁኔታ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መደንገግ አስፈላጊ መሆኑን የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሠረት ወልደሠንበት አስረድተዋል።

የክልሉ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ስርዓት ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ የክልሉን ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ባማከለ መልኩ ስርዓት መዘርጋት መሆኑን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

የቀረበውን የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የወጣውን ደንብ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቋል።

ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ