አትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ በ10 ኪሎ ሜትር የግሉን እና የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ

አትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ በ10 ኪሎ ሜትር የግሉን እና የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ

ሀዋሳ፡ የካቲት 09/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በስፔን ባርሴሎና በተካሄደ የፋክሳ ካስቴላኖ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ የግሉን እና የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፏል።

አትሌቱ ውድድሩን 26 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ በማጠናቀቅ ነው ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበው።

የገባበት ሰዓትም የርቀቱ የዓለማችን ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሲሆን ከአንድ ዓመት በፊት በሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ታደሰ ወርቁ ተይዞ ከነበረው የቦታው ክብረወሰን የተሻለ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል።

በሴቶች በተካሄደው ተመሳሳይ ርቀት ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በውድድሩ አትሌት መዲና ኢሳ 29 ደቂቃ ከ25 ሴኮንድ 1ኛ፣ አትሌት ልቅና አምባው 29 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ እንዲሁም አይናዲስ መብራቱ 30 ደቂቃ ከ05 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት 3ኛ ሆና በመግባት አጠናቀዋል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ