ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስልን 4ለ0 አሸነፈ

ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስልን 4ለ0 አሸነፈ

በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስል ዩናይትድን 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

ለማንቸስተር ሲቲ የማሸነፊያ ግቦችን ኦማር ማርሙሽ በ14ኛው፣24ኛው እና 33ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠር ሀትሪክ  መስራት ሲችል ቀሪዋን ግብ ተቀይሮ የገባው ጀምስ ማካቴ በ84ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

በማንቸስተር ሲቲ የመጀመሪያ ጎሎችን በ14 ደቂቃዎች ማስቆጠር የቻለው ማርሙሽ በእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመኑም የመጀመሪያ ሃትሪኩን ነው የሰራው።

ማንቸስተር ሲቲ በኤቲሀድ ስታዲየም ኒውካስልን በፕሪሚዬርሊጉ ለ16ኛ ተከታታይ ጊዜ ረቷል።

ማግፓይሶች ላለፉት 25 ዓመታት ሲቲዝኖችን ከሜዳቸው ውጪ ማሸነፍ አልቻሉም።

ማንቸስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 24 በማድረስ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ኒውካስል በ41 ነጥብ ወደ 7ኛ ደረጃ ተንሸራቷል።

በሌሎች ጨዋታዎች ፉልሃም ኖቲንግሃም ፎረስትን 2ለ1፣ቦርንማውዝ ሳውዝሃምተንን 3ለ1፣ብሬንትፎርድ ዌስትሃምን 1ለ0 አሸንፈዋል።

አስቶንቪላ እና ኢፕሲች ታውን ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ፕሪሚዬርሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ክርስቲያል ከኤቨርተን ይጫወታሉ።

በሙሉቀን ባሳ