አርሰናል ከሜዳው ውጪ ሌስተርን አሸነፈ

አርሰናል ከሜዳው ውጪ ሌስተርን አሸነፈ

በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ሌስተር ሲቲን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለሰሜን ለንደኑ ክለብ ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ሚኬል ሜሪኖ ከመረብ አሳርፏል።

አርሰናል በፕሪሚዬርሊጉ ያለመሸነፍ ጉዞውን ወደ 15 ጨዋታዎች አድርሷል።

መድፈኞቹ ቀበሮዎችን(ሌስተርን) በፕሪሚዬርሊጉ ለ7ኛ ተከታታይ ጊዜ ነው ማሸነፍ የቻሉት።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ በ53 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሌስተር በ17 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ፕሪሚዬርሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ማንቸስተር ሲቲ ከኒውካስል፣ፉልሃም ከኖቲንግሃም ፎረስት፣አስቶንቪላ ከኢፕስዊች ታውን፣ሳውዝሃምተን ከቦርማውዝ እንዲሁም ዌስትሃም ከብሬንትፎርድ ይጫወታሉ።

እንዲሁም ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ክርስቲያል ፓላስ ከኤቨርተን የሚገናኙ ይሆናል።

በሙሉቀን ባሳ