ስፖርታዊ ውድድሮች ለአገር ሰላምና አንድነት መጎልበት ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ገለፀ።
በልዩ ወረዳዉ ሲከናወን የነበረዉ የ2017 ዓ.ም ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድር ፍፃሜዉን አግኝቷል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጀዋር ጀማል በመርሃግብሩ ላይ እንዳሉት ስፖርታዊ ውድድሮች ለአገር ሰላምና አንድነት መጎልበት ሚናቸው ከፍተኛ ነው።
በዘርፉ የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ ልዩ ወረዳዉ ምቹ መሆኑን የገለፁት ሀላፊዉ ይህንን ለማጠናከር ቅንጅታዊ ስራዎች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።
በልዩ ወረዳዉ ሲከናወን የነበረዉ ስፖርታዊ ውድድር በስፖርታዊ ጨዋነት ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለፁት አቶ ጀዋር በክልል ደረጃ ለሚከናወነው ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድር የሚሳተፉ ስፖርተኞች ምልመላ መከናወኑንም ጠቁመዋል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ባለሙያ እና የልዩ ወረዳዉ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ አቶ አብድልከሪም ተማም በበኩላቸዉ በልዩ ወረዳዉ ሲከናወን የነበረዉ ስፖርታዊ ዉድድር በሰላም መጠናቀቁ ህብረተሰቡ ለዘርፉ የሰጠዉ ትኩረት ያሳያል ብለዋል።
በዉድድሩ በተለይ በወንዶች እግር ኳስ ልዩ ወረዳዉን የሚወክሉ ተጫዋቾች መመልመል መቻሉን የገለፁት አሰልጣኙ ቀጣይ በታዳጊ እና በአዋቂ የወንዶች እግር ኳስ ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራል ብለዋል።
ለዘርፉ ዉጤታማነት እንደ ዉስንነት የሚታዩ ከመጨዋቻ ሜዳ እና ሌሎች ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ አንስተዋል።
የዉድድሩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ስፖርት ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በተጨማሪ ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀው በዘርፋ የተሻለ ደረጃ ለመድረስ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
በዛሬዉ ዕለት በተከናወነዉ የወንዶች እግር ኳስ የፍፃሜ ዉድድር በእድገት በር ክላስተር ሌንጫ ዘቢሞላን፣ በወሸርቤ ክላስተር ወሸርቤ ቀቤና 2 ተኛን፣ በዉጥኝ ክላስተር ዉጥኝ ወለጌ ሱሙጌን በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል።
ዘጋቢ ፦ሪያድ ሙህዲን ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን በደርሶ መልስ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
ሊቨርፑል ዎልቭስን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ በ10 ኪሎ ሜትር የግሉን እና የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ