የመስኖ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የምርት ሽፋንን ለማሳደግ የላቀ ሚና አለው
ሀዋሳ፡ የካቲት 05/2017ዓ.ም (ደሬቴድ) በአከባቢው የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም አርሶ አደሩን በመስኖ የማልማት ባህል ለማዳበር እየተሠራ እንደምገኝ በኣሪ ዞን የዎባ ኣሪ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።
በተያዘው የበጋ መስኖ ከ700 በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አመላክቷል።
መንግስት የአርሶ አደሩን እርሻ ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ በአመት ሦስትና ከዚያ በላይ በማምረት የዜጎችን ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የሀገሪቱን የተረጅነት ገጽታ ለመቀየር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
በሀገሪቱ ከሚሰሩ ትላልቅ የመስኖ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በየአከባቢው የሚገኙ አነስተኛ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም የተለያዩ የግብርና ምርቶች እየለሙ ይገኛል። በኣሪ ዞን ዎባ አሪ ወረዳም ይህ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ማሳቸውን በመስኖ እያለሙ አግኝተን ያነጋገርናቸው የወረዳው አርሶ አደሮች ከዚህ ቀደም በመስኖ የማልማት ልምዳቸውን ገልፀው አሁን ላይ እያለሙ ካሉት ከ3 መቶ እስከ 5 መቶ ሺህ ብር ገቢ ለማግኘት አቅደው እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በወረዳው የቀበሌ ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለመጨመር ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።
የዎባ ኣሪ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሻው መካሪ እንደገለፁት በተያዘው የበጋ ወራት በየአከባቢው የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ከ7 መቶ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።
የዎባ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህዝቄል ጋርታ በበኩላቸው ወረዳው የወይና ደጋና ደጋ የአየር ፀባይ ያለበት በመሆኑ ማህበረሰቡ የዝናብ ወቅትን ብቻ ጠብቆ በአመት አንድና ሁለት ብቻ ያመርት ከነበረበት የበጋ መስኖን ጨምሮ በአመት ከሦስት በላይ እንዲያመርት በተደረገው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ አየታየ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከውጭ ይገቡ የነበሩትን ሰብሎች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው አስታወቁ