ፓትሪክ ቬራ ከጄኖኣ ሀላፊነት ተሰናበተ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ ከጄኖኣ ሀላፊነት ተሰናብቷል።
ዝነኛው የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ከጣሊያኑ ክለብ አሰልጣኝነት የተሰናበተው ደካማ ውጤት በማስመዝገቡ መሆኑ ተገልጿል።
አሰልጣኙ በዚህ የውድድር ዓመት በሴሪኣው 9 ጨዋታዎችን አከናውኖ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።
ጄኖኣ በሊጉ በ6 ጨዋታዎች ተሸንፎ ሦስት መርሐግብሮችን ደግሞ በአቻ ውጤት በማጠናቀቅ በ3 ነጥብ በሴሪኣው የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ይገኛል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 እግር ኳስ መጫወትን ካቆመ በኋላ ፊቱን ወደ አሰልጣኝነት ያዞሬው ቬራ ከዚህ ቀደም በአሜሪካው ኒውዮርክ ሲቲ፣ በእንግሊዙ ክርስቲያል ፓላስ እንዲሁም በፈረንሳዩ ስታራስቡርግ ያልተሳካ የአሰልጣኝነት ቆይታ እንደነበረው አይዘነጋም።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ቱርክ 149 የእግር ኳስ ዳኞችን አገደች
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 7 ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
ቼልሲ በሰንደርላንድ ሲሸነፍ ኒውካስል ፉልሃምን አሸነፈ