በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ በተከሰተ ሰደድ እሳት ከሃያ ስድስት ሄክታር መሬት በላይ ምርቶች ሙሉ በሙሉ መውደሙን የወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
በወረዳው አዲስ ቦዳሪ ቀበሌ ሾማ በተባለው አከባቢ የካቲት 04 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6 ሰኣት ላይ የተከሰተው ሰደድ እሳት በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
በቃጠሎው ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ባይደርስም ከ26 ሄክታር በላይ የሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ እንድሁም የማልማት አቅም ያላቸው የውሃ ማስተላለፊያ ፕላስቲክ ቱቦ እና ሌሎች ምርት ሙሉ በሙሉ ውድመት መድረሱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ኢንጅነር ዘለቀ ሲሳይ አስታውቀዋል ።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እና የፖሊስ አዛዥ እንዲሁም የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች የጉዳቱን መጠን ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፣ የሰደደ እሳት ከመስፋፋቱ በፊት በህብረተሰብ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ተናግረዋል ።
ወቅቱ የበጋ ወቅትና ደረቃማ የአየር ሁኔታ መኖሩን ተከትሎ ከሰል ማክሰልና በእርሻ ማሳ ላይ የሚሎከስ እሳት በተፈጥሮ ሀብት ላይ እያደረሰ ካለው ተጽዕኖ ባሻገር የሰደድ እሳትን የሚያስከትል ስለሆነ ህብረተሰቡ ከሰል ከማክሰል እና እሳት ከመልቀቅ መቆጠብ እንዳለባቸው አስተዳዳሪው አሳስቧል።
የደረሰው ጉዳት አሳዛኝ ነው ሲል የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው፥ የሰደድ እሳት መንስኤ በአግባቡ ተጣርቶ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
የጉዳቱ ሰላባ ከሆኑት መካከል አቶ አሰፋ ሶሬ እና አቶ አስረስ ሶሬ በሰጡት አስተያየት በተከሰተው አደጋ እጅግ ማዘናቸውን ገልጸው በብዙ ልፋትና በበርካታ ገንዘብ ወጥቶበት የለሙ በአንድ ደቂቃ አመድ መሆኑ በኢኮኖሚያቸው ላይ ትልቅ ጫና እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡
ሆኖም የሰው ህይወትና ጉዳት ከመድረሱ በፊት እሳቱን መቆጣጠሩ ትልቅ ትርፍ መሆኑንን ተናግረዋል።
ዘጋቢ : አሸናፊ ግዛው – ከዋካ ጣቢያች
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት