በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 7 ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
የ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት መካሄድ ሲጀምር 7 ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
የሊጉ መሪ አርሰናል በተርፍሙር ከበርንሌይ ጋር ከ12 ሰዓት ጀምሮ ይጫወታል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉ ባከናወናቸው ያለፉት ሦስት ጨዋታዎች፤ በሁሉም ውድድሮች ደግሞ በስድስት ጨዋታዎች ጎል ሳይቆጠርበት በማሸነፍ በጥሩ ወቅታዊ ብቃት ላይ ይገኛል።
በአሰልጣኝ ስኮት ፓርከር የሚመራው በርንሌይ በፕሪሚየር ሊጉ ከ2022 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ 2 ተከታታይ ጨዋታዎችን አሸንፎ ነው ከመድፈኞቹ ጋር ዛሬ የሚፋለመው።
ማንቸስተር ዩናይትድም ከሜዳው ውጪ በተመሳሳይ ሰዓት ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ይጫወታል።
ማንቸስተር ዩናይትድ 4ኛ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ወደ ሜዳ ይገባል።
ኖቲንግሃም ፎረስት በአንፃሩ ከአራት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማል።
ብራይተን ከሊድስ፣ ፉልሃም ከዎልቭስ እንዲሁም ክርስቲያል ፓላስ ከብሬንትፎርድ በተመሳሳይ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ደግሞ በለንደን ደርቢ ቶትንሃም ከቼልሲ የሳምንቱን ተጠባቂ ጨዋታ ያካሂዳሉ።
እንዲሁም ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ሊቨርፑል ከአስቶንቪላ በሌላ ተጠባቂ ጨዋታ ይፋጠጣሉ።
በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው ሊቨርፑል በፕሪምየርሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት 4 ጨዋታዎች ሽንፈትን ሲቀምስ አስቶንቪላ በአንፃሩ አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን ድል ማድረጉ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ቱርክ 149 የእግር ኳስ ዳኞችን አገደች
ፓትሪክ ቬራ ከጄኖኣ ሀላፊነት ተሰናበተ
ቼልሲ በሰንደርላንድ ሲሸነፍ ኒውካስል ፉልሃምን አሸነፈ