ቱርክ 149 የእግር ኳስ ዳኞችን አገደች
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሩቅ ምስራቋ ሀገር ቱርክ 149 የእግር ኳስ ዳኞችን ከጨዋታ ማገዷን አሳውቃለች።
የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን እንዳስታወቀው ዳኞቹ ላይ እገዳው የተጣለው በውርርድ ጨዋታ በመሳተፋቸው ነው።
ዳኞቹ ጥፋተኛ መሆናቸው መረጋገጡን ተከትሎ ከ8 እስከ 12 ወራት የሚደርስ እገዳ እንደተጣለባቸው ተገልጿል።
በእነዚህ የእግር ኳስ ዳኞች ላይ ለአምስት ዓመታት በተደረገ ምርመራ ከ571 ዳኞች መካከል 371 የሚሆኑት ውርርድ የሚያደርጉበት የግል የሂሳብ ደብተር እንዳላቸው ተነግሯል።
ከእነዚህም ውስጥ 152 የእግር ኳስ ዳኞች አዘውትረው ውርርድ እንደሚጫወቱ ተደርሶባቸዋል ነው የተባለው።
በቱርክ ሱፐር ሊግ ክለቦች በተደጋጋሚ በዳኞች ላይ ቅሬታ ሲያቀርቡ ይስተዋላል።
በዚህ ተቃውሞ የተነሳም ባለፈው ዓመት ጋላታሳራይ ከፌነርባቼ ያደረጉትን የእስታንቡል ደርቢ ጨዋታ ስሎቬኒያዊው ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺች በዋና ዳኝነት ጨዋታውን መምራቱ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ፓትሪክ ቬራ ከጄኖኣ ሀላፊነት ተሰናበተ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 7 ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
ቼልሲ በሰንደርላንድ ሲሸነፍ ኒውካስል ፉልሃምን አሸነፈ